የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ስልጠና ሰጠ

 የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ስልጠና ሰጠ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በከፍተኛ ትምህርት ስልጠና ተቋማት ትስስር፣ በምርምር ተቋማት፣ በኢንዱስትሪ ትስስር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በአዕምሮአዊ ንብረት ቁልፍ ርዕሶች ዙሪያ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮዎች እና ኢንዱስትሪዎች ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ በመስከረም 14/2014ዓ.ም ስልጠና ሰጥቷል::

ክቡር ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ በበየነ መረብ ባስተላለፉት መልዕክት ሀገራችን ከኢኮኖሚው አንጻር ያስቀመጠችውን መካከለኛ ገቢ ያላት ሀገር የመመስረት ራዕይ እውን ለማድረግ እና እየተመዘገበ ያለውን ዕድገት ቀጣይነት ለማረጋገጥ፣ የተሟላና የተሳካ ለማድረግ የቴክኖሎጂ አቅምን መገንባት ወሳኝ ነው ብለዋል:: ፕ/ር አፈወርቅ አክለውም ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማትም ለልማት የሚያስፈልጉንን ውጤታማ ቴክኖሎጂዎችን የማመንጨት፣ የመለየት፣ የማፈላለግ፣ የመምረጥ፣ የመጠቀም፣ የማላመድ እና ከኢንዱስትሪዎች ጋር የማስተሳሰር አቅማቸውን ማጎልበት እንዲሁም በቅርበት ተናበው መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል::

ዶ/ር አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የእውቀትና የቴክኖሎጂ ምንጭ በመሆን የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን በንድፈ ሀሳብና በተግባር እውቀት የተገነቡ፣ በገበያ ተፈላጊነት ያላቸው፣ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ እና ስራ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ከኢንዱስትሪዎች ጋር በጥብቅ ቁርኝት መስራት ሲችሉ እና የዩኒቨርሲቲዎች ስርዓተ ትምህርት ቀረጻም የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ መሆን አለበት ብለዋል::

ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው የአእምሮአዊ ንብረት አጠቃቀም ረቂቅ መመሪያን በማዘጋጀት ይፋ የደረገ ሲሆን ተመራማሪዎችም ከሚያመነጩት ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ የሚሆኑበት ስርዓት እየተዘረጋ መሆኑን ገልጸዋል::

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et