በሀዋሳ ዩ. ጤ ሳ. ኮ. ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተጋበዙ መምህራን የተግባር ምዘና ለተመራቂ ተማሪዎች በመከናወን ላይ ይገኛል።
የኮሌጁ ስኪል ላቦራቶሪ ማናጀር የሆኑት ረ/ፕ ኤፍሬም ጌጃ እንደገለፁት ከመስከረም 12, 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በመጡ ልምድ ባላቸው መምህራን የተግባር ምዘና /OSPE external exam/ ለነርሲንግ ትምህርት ቤት ተመራቂ ነርሲንግ ተማሪዎች በማከናወን ላይ ይገኛል። በተለይም በዩኒቨርሲቲያችን እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ጥራት ላይ ትኩረት ሰጥተን መስራት ላይ ባለንበት በዚህ ወቅት ዩኒቨርሲቲው የራሱን መምህራን በመጠቀም ከሚደርገው የተግባር ምዘና ጎን ለጎን ተመርቀው ወደ ስራ ገበታቸው ከመመደባቸው በፊት ይህን ዓይነት ምዘና ማድረግ ተገቢ እና አስፈላጊም ጭምር መሆኑን ገልፀዋል።