በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ለ7ኛ ጊዜ ተማሪዎቹን በመስከረም 9/2014 ዓ.ም አስመረቀ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ለ7ኛ ጊዜ ተማሪዎቹን በመስከረም 9/2014 ዓ.ም አስመረቀ።

ዶ/ር አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ለተማራቂዎቹ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት የዛሬ ተመራቂዎችም ወደ ስራ ዓለም ስትገቡ የሚያጋጥማችሁን ጊዚያዊ ችግሮችን ወደ መልካም አጋጣሚዎች በመቀየር መፍትሄን በመሻትና በአሁኑ ጊዜ ሀገራችንን እየፈተነ ያለውን የሰላም ዕጦት፣ የጥላቻና አድሎአዊነት አሰራር እንዲሁም የሙስና አስተሳሰብና ተግባርን በመጠየፍ፣ በሀገራዊ አንድነትና በወንድማማችነት በመቆራኘት ያስተማረንን ህብረተሰብ በመርዳት የሀገራችንን ሰላምና ብልጽግና ጉዞ ለማረጋገጥ የድርሻችሁን እንድትወጡ አደራ ለማለት እወዳለሁኝ፡፡

የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት ክቡር አቶ በየነ በራሳ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ርዕሰ መስተዳድር እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ እንደተናገሩት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ውስብስብና ተደራራቢ ጫና በበዛበት ወቅት ላይሆኖ የመማር ማስተማር፣ የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራውን ያለአንዳች መስተጓጎል አጠናክሮ በመቀጠል ለዚህ ስኬት መብቃቱ የአመራሩን እና የመላ ሰራተኞቹን ቁርጠኝነትና ትጋት የሚያሳይ ከመሆኑም በተጨማሪ በእጅጉ የሚያስመሰግነው ነው ብለዋል፡፡

አቶ በየነ በራሳ አክለውም እንደገለጹት ተመራቂዎችም ስራ ፈጣሪዎች እንጂ ስራ ፈላጊ ዜጎች ብቻ ሳትሆኑ የራሳችሁንም ስራ በመፍጠር ሌሎችን ቀጥራችሁ በማሰራት ለራሳችሁም ሆነ ለሀገራችሁ የበኩላችሁን ሚና መጫወት የምትችሉ ዜጎች ጭምር መሆን  ይኖርባችኃል ብለዋል፡፡

የአዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ወገኔ ማርቆስ እንደተናገሩት ኮሌጁ በዛሬው እለት 598 በመጀመሪያ ዲግሪ እና 11 በሁለተኛ ዲግሪ በድምሩ 609 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ተመራቂ ተማሪዎችም እራሳችሁን የመፍትሄ ሰው በማድረግ ትልቅ አደራ ከሀገር እና ከቤተሰብ እንደሚጠብቃችሁ ተገንዝባችሁ በሰለጠናችሁት ሙያ ሀገራችሁን በትጋትና በታማኝነት በማገልገል ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ እያሳሳብኩኝ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁኝ ብለዋል፡፡

 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et