የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ወንዶገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ለ42ኛ ጊዜ ተማሪዎችን አስመረቀ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ወንዶገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ለ42ኛ ጊዜ ተማሪዎችን አስመረቀ።

በመስከረም6/ 2014ዓ.ም ዶ/ር ሞቱማ ቶሌራ የወንዶገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ዲን በዕለቱ እንደተናገሩት ኮሌጁ ከ40 ዓመታት በላይ በደንና ተፈጥሮ ሀብት መርሓ ግብሮች በተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች ተማሪዎችን በማሰልጠን ሀገሪቷ የምትፈልገውን ባለሙያ በማበርከት ላይ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በመጀመሪያ ዲግሪ በ12፣ በሁለተኛ ዲግሪ በ13 እንዲሁም በሶስተኛ ዲግሪ በ2 የትምህርት ዘርፎች ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ላይ እንደሚገኝ ገልጸው በዛሬው ዕለትም በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 505 ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ከእነዚህም ውስጥ 35 ፐርሰንት የሚሆኑት ሴት ተመራቂዎች ናቸው ብለዋል::

ዶ/ር አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ለተመራቂዎቹ ባስተላለፉት ንግግር በዓለማችን ብሎም በሀገራችን በተከሰተው ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተማሪዎች መመረቅ ከሚገባችሁ ጊዜ የዘገያችሁ ቢሆንም ባደረጋችሁትና ባደረግነው ከፍተኛ ተጋድሎ በዚህ አኳሃን ለመመረቅ በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል::

ዶ/ር አያኖ አክለውም ውድ ተመራቂዎችም ወደሥራ ስትገቡ የሚያጋጥማችሁን ጊዚያዊ ችግሮችን ወደ መልካም አጋጣሚዎች በመቀየር በአሁኑ ጊዜ ሀገራችንን እየፈተነ ያለውን የሰላም ዕጦት፣ የጥላቻና አድሎአዊነት አሰራርን በመጠየፍ፣ በሀገራዊ አንድነትና ወንድማማችነት በመቆራኘት ያስተማረንን ህብረተሰብ በመርዳት የሀገራችንን ሰላምና ብልጽግና ጉዞ ለማረጋገጥ የየድርሻችሁን እንድትወጡ አደራ እላለሁኝ::

የዕለቱ የክብር እንግዳ ክቡር አቶ ከበደ ይማም የኢፌድሪ የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር በዕለቱ ባስተላለፉት መልእክት የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎችን ምርቃት የተለየ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ ሀገራችን የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብርን ዋነኛ የልማት አጀንዳዋ አድርጋ የተንቀሳቀሰችበት ያለችበትና ይልቁንም የተጀመረውን በጎ አሻራን የማኖር ሥራ ወደ ጎረቤት ሀገራት ለማስፋት ከፍተኛ ርብርብ እያደረገችበት ባለችበት ጊዜ መሆኑ ነው ብለዋል::

ኮሚሽነሩ አክለውም ኮሚሽን መሥሪያ ቤታችን የወንዶ ገነት የደንና የተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ በዘርፉ የልህቀት ማዕከል እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ ከዚፈ በፊት ያደረገና ወደ ፊትም እንደሚያደርግ እየገለጽኩ የዛሬ ተመራቂዎች በዚህ ዘርፍ በመመረቃችኹ ኩራት ሊሰማችሁ ይገባል እያልኩ በምትሄዱበት አካባቢ ሁሉ ሀገራችንን አረንጓዴ በማልበስ ድርሻችኹን እንድትወጡ አደራ እላለኹኝ ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል::

 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et