የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሀዋሳ ከተማ ለሚገኙ ቁጥራቸው ከ150 በላይ ለሚሆኑ ስራ -አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል እንዲፈጠር አደረገ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴ/ሽ/ም/ፕሬዝዳንት ስር የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ለስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጥሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በጎዳና ላይ ለሚገኙ 150 ስራ አጥ ወጣቶች ስራ ፈጠራና ገቢ ማመንጫ የሚሆን የጫማ ማስዋቢያ ሊስትሮ ዕቃ ከነሙሉ ግብዓት እንዲሁም ለተደራጁ ስራ አጥ 3 ማህበራት የዛፍ ችግኞችን ጷጉሜ 4 ቀን 2013 ዓ.ም የሀዋሳ ከንቲባ በተገኙበት ርክክብ አደረገ፡፡

አቶ ጸጋዬ ቱኬ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ በዕለቱ እንደገለጹት በዓለም ላይ ብቸኛ የመለወጫና የማደጊያ እንዲሁም ሰውን የሚያስከብረው መንገድ ስራና ስራ ብቻ በመሆኑ ድጋፍ የተደረገላችሁ ወጣቶችም የተፈጠረላችሁን ይሄንን ዕድል በመጠቀም እራሳችሁን ለውጣችሁ  በስራችሁ ውጤትም ለሌሎች ምሳሌ በመሆን ለራሳችሁ፣ ለማህበረሰባችሁ እና ለሀገራችሁ ጠቃሚ ዜጋ እንድትሆኑ እያሳሰብኩኝ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲም ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመሆን ይሄንን መሰሉን ድጋፍ በተለያየ ጊዜ እያደረገ በመሆኑ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁኝ ብለዋል፡፡

ዶ/ር አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሁልጊዜም ዩኒቨርሲቲው በሚሰራቸው የመማር ማስተማር፣ በምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎትና በስራ ዕድል ፈጠራ ስራዎቹ  የአካባቢውን ማህበረሰብ እየደገፈና ወደፊትም የሚደግፍ መሆኑን በመግለጽ ወደፊትም ለሌሎች ስራ አጥ ወጣቶች ስልጠና በመስጠት ወደስራ እንዲገቡ  እና ነጻ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ታፈሰ ማቴዎስ የምርምርና ቴ/ሽ/ም/ፕሬዝዳንት እንደገለጹት ለ150 ስራ አጥ ወጣቶች ስልጠና በመስጠት ስራ ለመጀመር የሚያስችል  በአንድ ግዜ ሶስት ተገልጋዮችን ለማስተናገድ የሚስችሉ 50 ሼዶችን፣ ሊስትሮና ቀለም እንዲሁም ለተደራጁ 25 ወጣቶች በከተማ አበባ ልማትና ማስወብ እነዲሰማሩ ሙሉ ግብዓት ዩኒቨርሲቲው ማሟላቱን እና ለዚህም ከ1.2 ሚሊ. ብር በላይ ወጪ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et