የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ለኮሌጁ አመራሮች ስልጠና ሰጠ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ በአዲሱ የስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና አዋጅ እና በዕቅድና ሪፖርት አዘገጃጀት ላይ ለኮሌጁ አመራሮች ስልጠና  እና ከዚሁ ጋር በተያያዘም የኮሌጁ የ2013ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም  ላይ ግምገማ  ከሐምሌ 12 -14/2013ዓ.ም ድረስ  ለሶስት ተከታታይ ቀናት አደረገ ፡፡

አቶ በላይ በልጉዳ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ማኔጂንግ ዳይሬክተር በመክፈቻው ላይ እንደገለጹት የኮሌጁን አመራሮች አቅም ለማጎልበት  በስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና አዋጅና አደረጃጀት እና በዕቅድና ሪፖርት አዘገጃጀት ላይ አዲስ አሰራር በመኖሩ ወደፊት የተሻሉ ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሆኑን ገልጸው አመራሮችም ያሉብንን ክፍተቶች በመራዳትና በመሙላት እንዲሁም በየክፍሎቻችን ያሉትን ፈጻሚዎች በማብቃት በቀጣይ ወደተሻለ አፈጻጸም ደረጃ መድረስ ይኖርብናል ብለዋል፡፡

አቶ ከበደ ኩማ የስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  እንደተናገሩት በሀገራችን አሁን እያየን ያለነው ተግዳሮቶች የዜጎች የመልካም ምግባርና የሞራል ዕሴት መፈራረስ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ዕጦት  ውጤት በመሆኑ ሁላችንም በዚህ ዙሪያ ተረባርበን የድርሻችንን በመወጣት ሀገራችን እያሳየችው ላለው ዕድገት እና የለውጥ ጎዳና አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙም ላይ በመልካም ምግባርና የሞራል ግንባታ፣ በአዲሱ የስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና አዋጅ፣ በዕቅድና ሪፖርት አዘገጃጀት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከተሰጠ በኃላ የኮሌጁ አራት የአካዳሚክ ክፍሎች የ2013ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም  ቀርቦ ውይይትና ገንቢ አስተያየቶች ተሰጥቶባቸው ፕሮግራሙ መጠናቀቁ ታውቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et