የአፈር ጥበቃና የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ በምዕራብ አርሲ ሻላ ወረዳ ተካሄደ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በኦሮሚያና በሲዳማ ክልሎች አዋሳኝ ቦታ ላይ ከምዕራብ አርሲ ሻላ ወረዳ አልጌርሚ ቀበሌ ነዋሪዎችና አርሶ አደሮች እንዲሁም ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር በመተባበር በምዕራብ አርሲ ሻላ ወረዳ አልጌርሚ ቀበሌ የአፈር ጥበቃና የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ሐምሌ 6 ቀን 2013 ዓ.ም ለ4ኛ ጊዜ አካሄዷል፡፡

ዶ/ር መሳይ ሀይሉ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ከወረዳው ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት በአካባቢው አፈርና የተፈጥሮ ሀብት በጎርፍ ተጠርጎ እንዳይወሰድ ለማድረግ፣ የሀዋሳ ሀይቅ በደለል እንዳይሞላ ከመታደግ እና የአረንጓዴ አሻራን ከማስቀጠል አኳያ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ተጠንተው በተዘረጋው ስርዓት መሰረት በባለፈው የበልግ ወቅት በርካታ ስራዎች ተሰርተው ወደ ሀይቁ የሚገባውን 8 ሺህ ሜትር ኪዩብ አፈር ለመያዝ መቻሉን ገልጸው ወደፊትም የመከላከል ስራዎችን ለማስቀጠል ዩኒቨርሲቲው ድጋፍና ክትትል በማድረግና የተሻሻሉ የምርምር ቴክኖሎጂዎችንና ውጤቶችን እንደሚስተዋውቅ ተናግረዋል፡፡ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ ሲናገሩ የዚህን መሰሉ የአፈር ጥበቃ ስራዎች ከዚህ በፊት በሲዳማ ክልል በበርቻ ወረዳ እና ኤዶ ላይም በመስራት ውጤታማነታቸው የተረጋገጠ ሲሆን የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራዎች በዘመቻ ብቻ ሰርተን የምንተወው ሳይሆን ወደፊትም አቅደን ሳናቋርጥ የምንሰራቸው ስራዎች መሆን ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et