የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ

በአዲስ መልክ የተዋቀረው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ወደ ሥራ ለመግባት ባካሄደው ስብሰባ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ ስለዩኒቨርሲቲው አጭር ገለጻ በማቅረብ ለአዳዲሶቹ የቦርዱ አባላት ግንዛቤ ያስጨበጡ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ዩኒቨርሲቲው በምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ተርታ ከመፈረጁም ጋር አዲስ አባላት ወደ ሥራ አመራርነት በመቀላቀላቸው የተሰማቸውን ደስታ መግለጻቸው ታውቋል፡፡

ይህን ተከትሎ ቦርዱ የ2013 በጀት ዓመት የ9 ወር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ግምገማ ያካሄደ ሲሆን የተነሱ ጠንካራ ጎኖች ጎልብተው እንዲቀጥሉና የታዩ ክፍተቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ማስተካከያዎች እንዲደረጉ በቦርዱ አባላት ሀሳብ ተሰንዝሯል፡፡ በመጪው የ10 ዓመት ስትራቴጂ ዕቅድ ላይም ጥልቅ ውይይት በማድረግ ዩኒቨርሲቲው የምርምር ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ መጠን ለወሳኝ መሠረተ ልማቶች ተገቢ ግብዓት እንዲሟላ በቀጣይነት ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስ ባለበት አቅጣጫዎች ላይ ቦርዱ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡ እንዲሁም አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ በየደረጃው ያሉ አመራር አካላት የላቀ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አጽንኦት በመስጠት መሥራት እንደሚገባ በመስማማት ስብሰባው ተጠናቋል፡፡ 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et