የትምህርት ኮሌጅ የ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የምርምር ግምገማ አካሄደ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ኮሌጅ ከመጋቢት 24-25/2013ዓ.ም ድረስ ዓመታዊ የምርምር ግምገማ በዋናው ግቢ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ አካሂዷል፡፡ ዶ/ር አብርሃም ቱሉ የትምህርት ኮሌጅ ዲን ኮሌጁ 5 የሶስተኛ፣ 7 የሁለተኛ፣ 13 የመጀመሪያ

ድግሪ እና 4 የሰርቲፊኬት ፕሮግራሞችን በመክፈት ከሁለት ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረና ከእነዚህም  ውስጥ 320 የድህረ ምረቃ ተማሪዎች መሆናቸውን ገልጸው የኮሌጁ መምህራንም በትምህርት ጥራት ላይ እያጋጠሙ ባሉ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው ላይ ወቅቱን የጠበቀ ችግር ፈቺ ምርምሮችን እየሰሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ከ20 የሚበልጡ ተመራማሪዎች ምርምር እያካሄዱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ አክለውም ተመራማሪዎችም የሰሯቸውን የምርምር ውጤቶች የተለያዩ ሚዲያዎችንና ማህበራዊ ድረ ገጾችን በመጠቀም ለሳይንሱ ማህበረሰብ ተደራሽ ማድረግ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይም ማሳተም እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት በመክፈቻ ንግግራቸው ለሀገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት ትምህርት ቁልፍ መሳሪያ በመሆኑ ሀገራችንን ማሳደግ ከፈለግን በትምህርትና ትምህርት ጥራት ላይ በርትተን መስራት ይኖርብናል ያሉ ሲሆን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲም የምርምር ዩኒቨርሲቲ ተብለው ከተለዩት አንዱ እንደመሆኑ ምርምር ላይ ትኩረት ሰጥተን ለመስራት መምህራኖቻችንን በምርምር እንዲሳተፉ ማድረግና አቅማቸውንም ማጎልበት፣ የምርምር ፕሮጀክቶችን መገምገም፣ አዳዲስ የምርምር ጆርናሎችን ማቋቋም፣ የምርምር ውጤቶች በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ እንዲወጡ ማድረግና የምርምር ፕሮጀክቶችንም ከድህረ ምረቃ ተማሪዎች ጋር            ማስተሳሰር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

በሁለቱ ቀናትም የተለያዩ ተመራማሪዎች የሰሯቸውን የምርምር ውጤቶች ካቀረቡ በኃላ ውይይት ተደርጎባቸው ፕሮግራሙ መጠናቀቁ ታውቋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et