በምር/ቴክ/ሽግ/ም/ፕ/ጽ/ቤት የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በሲዳማ ክልል ወንዶገነት ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች ምርጥ ዘሮችን አበረከተ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬ/ጽ/ቤት በማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት አማካኝነት መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በተመረጡ ወረዳዎች የተለያዩ የሰብል እና እንስሳት ቴክኖሎጂዎችን ለተጠቃሚዎች የማስተዋወቅና

ተጠቃሚ የማድረግ ስራዎች እየሰራ ሲሆን በሲዳማ ክልል ወንዶ ገነት ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የእርሻ ምርትና ምርታማነት እንዳይቀንስ መንግስት እየሠራ ያለውን ሥራ ለመደገፍና አዲስ ዝርያዎችን ለማላመድ የተሻሻለ የፕሮቲን በቆሎ ዝርያ አበረከተ፡፡ ዶ/ር ፍሬው ካሱ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንደተናገሩት ይህ የበቆሎ ዝርያ ፖይነር በመባል የሚታወቅ ሲሆን ከሌሎች የበቆሎ ዝርያዎችም የሚለየው የፕሮቲን ይዘት ያለው በመሆኑ ተመጋቢዎች ከእንስሳት ተዋጾዎች የሚያገኙትን ፕሮቲን በዚህ የበቆሎ ዝርያ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡ ዶ/ር ፍሬው አክለውም ይሄንን የበቆሎ ዝርያ ከወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት ጋር በመሆን በወተራና ቀጨማ፣ አሩማ እና ዩዎ ሶስት ቀበሌዎች ለሚገኙ 32 አርሶ አደሮች መከፋፈሉንና ከዚህ በፊትም በተያዘው ዓመት በመኸር የሚዘራ 10 ኩንታል ሹሩሜ በመባል የሚታወቅ ስንዴ ዝርያ እና ኢቦኒ የሚባል የገብስ ዝርያ እንዲሁም የተሻሻለ የቦንጋ የበግ ዝርያ ለአርሶ አደሮች መከፋፈሉን ገልጸው አርሶ አደሮችም የተሰጣቸውን የበቆሎ ዝርያ በአግባቡ በመዝራት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንዳለባቸውና ሌሎች አርሶ አደሮችም ይሄንን ልምድ በመቅሰም የማስፋትና የማላመድ ስራዎችን መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et