የወንዶ ገነት ደንና የተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ እና ጂኦ ፋሻል ኢንፎርሜሽን ሴንተር በተለያዩ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

ስምምነቱ የተቋማቱን የረጅም ጊዜ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሳድገው የተገለጸ ሲሆን የወንዶ ገነት ደንና የተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሞቱማ ቶለራ በስምምነቱ ወቅት እንደገለጹት ኮሌጁ ከ40 ዓመታት በላይ የማስተማር ልምድ ያለው

ሆኖ በአከባቢ ጥበቃ፣ በአየር ንብረት ለውጥና በአሬንጓዴ ልማት ስራዎች በርካታ ባለሙያዎችን በማሰልጠንና ወደ ስራ በማሰማራት ሀገራዊ ግዴታዉን እየተወጣ ያለ ተቋም መሆኑን አስረድተዋል፡፡ አያይዘውም ኮሌጁ በአሁኑ ሠዓት በ12 የትምህርት ክፍሎች ከመጀመሪያ እስከ PHD በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን እያስተማረ መሆኑንም በመግገለፅ በቅርቡም የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ባወጣዉ ድልድል መሠረት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሣይንስና ምርምር ማዕከልነት ከተደለደሉ አንጋፋ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ በመሆኑ ኮሌጁም ይህን  መሠረት ባደረገ መልኩ ከተለያዩ  መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እንደ ዶ/ር ሞቱማ ቶለራ ገለፃ ኮሌጁ በአሁኑ ሰዓት በደንና አከባቢ ጥበቃ (Agroforestry)፣ አሬንጓዴ ልማትና ዘመናዊ የመሬትና ካርታ ስራና ንባብ (GIS) ዘርፎች በትኩረት እየሰራ ሲሆን ዉጤታማ ስራዎች እንዲሰሩ ጆኦ ፋሻል ኢንፎርሜሽን ሴንተር  ከዚህ ቀደምም በተግባር ስልጠና፣ በልምድ ልዉዉጥ፣ በገንዘብና ቁሳቁስ በርካታ ድጋፎችን ማድረጉም ተመላክቷል፡፡ የጂኦ ፋሻል ኢንፎርሜሽን ሴንተርን ወክለዉ በስምምነቱ ላይ የተገኙት ዶ/ር ቱሉ ባሻም በበኩላቸዉ እንደገለፁት ተቋሙ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ  ወንዶ ገነት ደንና የተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ጋር ለረጅም ጊዜያት በትብብር ሲሰራ መቆየቱን በመጠቆም ይህም ስምምነት የተቋማቱን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግርም ገልፀዋል፡፡

ስምምነቱን ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስትትዩትና ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር መፈራረማቸዉንም ዶ/ር ቱሉ የገለፁ ሲሆን ከአንጋፋዉ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ወንዶ ገነት የደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ጋር ሶሰተኛዉን ስምምነት በመፈራረማቸዉ ደስተኛ መሆናቸዉንም አስታዉቀዋል፡፡ ዘርፉን በምርምርና ቴክኖሎጂ ከማዘመንም ባሻገር በሰዉ ሃይል ስልጠና ፈጣንና ቀልጣፋ የመረጃ ልዉዉጥ ስራዎችም በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et