የአዳዲስ  ጆርናሎችን መተግበሪያ ረቂቅ ሰነዶች ላይ ውይይት ተካሄደ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አዳዲስ ለሚመሰረቱት የምርምር ጆርናሎች የሚጠቅሙ የምርምር ስነ ምግባር እና የአዕምሯዊ ንብረት መብት ረቂቅ ሰነዶች ላይ ለሁለት ቀናት ማለትም ከታህሳስ1-2/2013ዓ.ም ድረስ ከተለያዩ ምሁራን ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት በመክፈቻው ላይ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመበት ዕድሜና ካስቀመጠው ራዕይ አንጻር߹ በኢትዮጵያ ካሉት የመጀመሪያ ትውልድ ተቋሞች ውስጥ አንዱ እንደመሆኑ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ እንደመሆኑ ከዚህ በፊት የነበሩት ሁለት የሳይንሳዊ ምርምር ጆርናሎች የምርምር ውጤት የህትመት ቁጥሮችን ለማሳደግ በቂ ባለመሆናቸው ተጨማሪ ጆርናሎችን መመስረት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር ታፈሰ አክለውም ዩኒቨርስቲያችን ረጅም የምርምር ታሪክ ቢኖረውም መሰረታዊ߹ ግልጽ߹ ሳይንሳዊና ዘላቂ የምርምር ስነ ምግባርና የአእምሯዊ ንብረት መብት ደንቦችና መመሪያዎች ባለመኖራቸው ዩኒቨርሲቲውም ሆነ ተመራማሪዎቹ በቂ በሚባል ደረጃ ተደራሽና ተጠቃሚ ባለመሆናቸው ይህ የውይይት መድረክ የተዘጋጀ ሲሆን በውይይቱም ያለንበት ደረጃ ምን እንደሚመስል߹ ከዚህ በፊት የነበሩትን ጆርናሎች ተሞክሮ ምን እንደሚመስል߹ ሳይንሳዊ ጆርናል ምን ምን ነገሮችን ማሟላት እንዳለበት እና በሚቀርቡት ሰነዶች ላይ በጥልቀት በመወያየት በስተመጨረሻም ለአዳዲሶቹ ጆርናሎች የምስረታ ሰነድ ማዘጋጀት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙም ላይ ከሰነዱ አቅራቢዎች ትክክለኛውን ሳይንሳዊ የምርምር መመሪያዎችን ተከትሎ የምርምር ጆርናሎችን መመስረት እንዲሁም በዚያ ጆርናል ላይ የሚወጡና የሚታተሙ የምርምር ውጤቶች ምን ማሟላት እንዳለባቸው ማስቀመጥ ምርምሮቹ በሀገሪቱ ላይ በሚወጡ ፖሊሲዎች ላይ አበርክቶና ተጽዕኖ እንዲኖራቸው߹ አለም አቀፍ ሳይንሳዊ እውቀት ለማበርከት߹ ተፎካካሪና ለማህበረሰቡ ችግር ፈቺ ምርምሮችን ለማበርከት እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማሳደግ እንደሚረዳ የተገለጸ ሲሆን በተቃራኒው በትክክለኛው መመሪያ የማይሠሩ ምርምሮች ከጤና߹ ከማህበረሰብ߹ ከኢኮኖሚ ከመሳሰሉት አኳያ በርካታ ቀውሶችን እንደሚያስከትሉ በስፋት ተዳሰዋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et