በደቡብ ክልል ስላለው የመስኖ አቅም የጥናት ውጤት ይፋ ተደረገ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ የውሃና ውሃ ነክ ስራዎች አማካሪ ዩኒት ከክልሉ የውሃና መስኖ ልማት ቢሮ የመስኖ ግንባታና የተቋማት አስተዳደር ኤጀንሲ የቀረበለትን  የክልሉን የመስኖ አቅም ጥናት ጥያቄ ተቀብሎ

በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ባሉ ተመራማሪዎች ላለፉት ሁለት አመታት በክልሉ በሚገኙ አራት ዋና ዋና ተፋሰሶች ማለትም ባሮ አኮቦ ፣ገናሌ ዳዋ፣ኦሞ ግቤና ሬፍት ቫሊ ላይ ሰፊ ጥናትና አስፈላጊውን መረጃ በመሰብሰብ የጥናቱን የመጨረሻ ውጤት ለባለድርሻ አካላት በ06/10/2012ዓ.ም ይፋ አደረገ፡፡

አቶ አንተነህ ፍቃዱ በደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪና የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ በመክፈቻ ንግግራቸው እየገጠመን ካለው የአየር ንብረት መዛባት በተጨማሪ ዝናብን እየጠበቁ ከማረስና ከማምረት በመላቀቅ በብዛ ህይወታችን ላይ ለመመስረት የዚህ መሰሉን አይነት ጥናት አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ ጥናቱንም  በመመርኮዝ  እርሻዎቻችንን ወደ መስኖ በማስገባት እራስን በምግብ መቻል ብቻ ሳይሆን ለኢንዱስትሪ ግብዓት ጭምር ልናመርትና እንዲሁም ያመረትነው ላይ እሴት በመጨመር ወደ ውጭ እንድንልክ የዚህ መሰሉ ጥናት በብዛትና በጥራት ያስፈልጉናል በማለት አጥኚ ቡድኑንም አመስግነዋል፡፡

አቶ አሸናፊ ሽብሩ የክልሉ መስኖ ግንባታናተቋማት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ላለፉት ሁለት አመታት በክልሉ በሚገኙ አራት ዋና ዋና ተፋሰሶች እነዚህ ተፋሰሶች በሚያካልሏቸው ዞኖች፣ልዩ ወረዳዎችና ወረዳዎች አስፈላጊውን መረጃ በመሰብሰብ የመስኖ አቅም ልየታ ዶክመንት ለማዘገጀት የተደረገው ጥረትን አድንቀው በክልሉ የመስኖ ልማት ስራ ከተጀመረ የቆየ ቢሆንም በመስኖ የለማ ማሳ መጠን አነስተኛ እና ብዙ ማነቆዎች እንደነበሩበት ገልጸው ይሄ የጥናት ውጤት ግን በርካታ ነገሮችን ነገሮችን ይቀርፍልናል ብለዋል፡፡

በዕለቱም የተለያዩ ጥናቶች ቀርበው እና እስከ አሁን በገጸ-ምድርና ከርሰ-ምድር የውሃ ሃብት በመስኖ  የለሙ እና ወደፊትም የሚለሙ የእርሻ መጠን የተገለጹ ሲሆን  ከተሳታፊዎች ጋርም ውይይት ና ምክክር የተደርጎባቸው ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et