የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ በቴክኖሎጂ በመታገዝ በሁለት ሰነዶች ላይ ውጫዊ ግምገማ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ በቴክኖሎጂ በመታገዝ በሁለት ሰነዶች ላይ ውጫዊ ግምገማ በ10/10/12ዓ.ም አደረገ፡፡

ዶ/ር ኢ/ር ፍስሃ ጌታቸው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው በኢትዮጲያ ውስጥ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ተብለው ከተመረጡት ጥቂት ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በሁለት ሰነዶች ላይ ማለትም በመሬትና የአካባቢ ህግ ስርዓተ ትምህርትና በመሬት ስሪት እና አካባቢ መብት ጥናት ማዕከል መቋቋሚያ ሰነዶች ውጫዊ ግምገማ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቴክኖሎጂ በመታገዝ ቀጥታ (online) እየተወያየን እና የሚሰጡ እርምቶችንም በመያዝ መስተካከል ያለባቸውን በማረም ለቀጣይ በማዳበር ወደ ስራ እንገባለን ብለዋል፡፡

አቶ ጸጋዬ ቱኬ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ዲን ዩኒቨርሲቲው ሶስት አላማዎች በመያዝ ማለትም መማር ማስተማር ߹የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር እና የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት መሆኑን አስታውሰው በተነሱት ርዕሶች ላይ የቀጥታ ውይይት በማድረግ እና ሃሳቦችን በማዳበር በቀጣይ ተማሪዎቻችንን ለማስተማር እና የአካባቢውን ማህበረሰብና  ተቋማት በምርምር በታገዘ መልኩ ለማገዝ የሚረዳን ሲሆን የጥናት ማዕከሉ መቋቋም ደግሞ የተለያዩ ጥናቶችን ከመስራት በዘለለ መልኩ ወደህብረተሰቡ  ወርደን ለመስራት ያስችለናል ብለዋል፡፡

ዶ/ር ዳንኤል በሃይሉ የሕግ መምህርና ተመራማሪ ውይይቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን߹ከደንና የአየር ንብረት ߹ከኢትዮጲያ አካባቢ ጥበቃ እና ባለድርሻ አካላት ምሁራን ጋር የሚደረግ መሆኑን ገልጸው ከሰነዶቹ ግምገማ በመነሳት የግብርና ስራዎችን ለማስተሳሰር߹ህግ አውጪዎችም ህግን ሲያወጡ ነባራዊ ሁኔታዎችን እንዲያጤኑና ተግባራዊ እንዲያረጉ߹ተማሪዎችን በጥራት ለማስተማር ߹ማህበበረስብ ተኮር ስራዎችን ለመስራት እና ከዚህ በፊት የነበረው የመሬት ህግ ማህበረሰቡን የሚያጋጭ ስለሆነ እሱን ለመፈተሸ  እና ማህበረሰቡ በባህልና በወግ የሚያውቀውን ነገር በህግ ለማስተሳሰር ይረዳል ብለዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et