የኢትዮጵያ ደን ልማት ለወንዶገነት ደ/ተ/ሃ/ኮሌጅ ድጋፍ አበረከተ

የኢትዮጵያ ደን ልማት ለወንዶገነት ደ/ተ/ሃ/ኮሌጅ የልህቀት ማዕከል የሚያደርገው ድጋፍ አበረከተ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ለዳታ ማዕከሉ ማጠናከሪያ የሚሆኑ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው የመረጃ ቋት ማጠራቀሚያ፣ ከ60 በላይ ስክሪን ቦርዶች፣ ለረዥም ሰዓታት የሚያገለግሉ ባትሪዎችና ሌሎች መሳሪያዎች ግንቦት 24/2016 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ደን ልማት ተበርክቶለታል።

የኢትዮጵያ ደን ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሞቱማ ቶሌራ መሳሪያዎቹ የተገዙት ከኖርዌይ መንግስት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP-Ethiopia) እና CIFOR-ICRAF ከተባለ አጋር ተቋም በተደረገለት የቴክኒክ ድጋፍ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ ኮሌጁ የደንና ተፈጥሮ ሃብት ዘርፍን ሳይንሳዊ መረጃ ማዕከል ለማዘመንና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሟላ የደን እዉቀት አስተዳደር የልህቀት ማዕከል እንዲሆን በርትቶ እንዲሰራ አሳስበዋል። ዶ/ር ሞቱማ መሳሪያዎቹን ለኮሌጁ ዲን ጽ/ቤት ተወካይ ዶ/ር በየነ ተክሉ እና ለማኔጂንግ ዳይሬክተሩ አቶ በላይ በልጉዳ በይፋ አስረክበዋል::

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ውጭ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር: የኮሌጁ የስራ ኃላፊዎች: ተመራማሪዎች እና የአጋር ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት በዚሁ የርክክብ ወቅት የምስጋና ፕሮግራም እና በቀጣይ የመሳርያዎቹን ድጋፍ ተከትሎ ምን መሰራት እንዳለበት ምክክር ተደርጓል::

ዶ/ር በየነ ተክሉ የደንና ተያያዥ ዘርፎች ላይ ለሚደረጉ ሃገራዊና ክልላዊ አስተዋፅኦዎች በኢትዮጵያ ደረጃ እስካሁን ብቁ ምሁራንን በማፍራትም ሆነ ምርምሮችን በመስራት የወንዶገነት ደ/ተ/ሃ/ኮሌጅ ግንባር ቀደም ተዋናይ ቢሆንም ከዚህ የበለጠ መስራትና የልህቀት ማዕከል እንዲሆን የሚያስችለውን በጣም አስፈላጊ ግብዓት ላበረከተው የኢትዮጵያ ደን ልማት መስሪያ ቤት እና ለአጋር ድርጅቶች ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል:: ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ አቶ በላይ በልጉዳ በበኩላቸው ለኮሌጁ በተበረከተዉ ድጋፍ እጅግ ደስተኛ መሆናቸዉን ገልፀው ትብብሩን ቀጣይነት እንዲኖረው የሁሉም አካላት ድርሻ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et