አቀፍ የልህቀት ማዕከል ለመመስረት ዉይይት ተካሄደ

የወንዶገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ሀገር አቀፍ የልህቀት ማዕከል ለመመስረት ከኢትዮጰያ ደን ልማት ጋር ዉይይት አካሄደ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ደን ልማት ጋር በመተባባር 'የደን እዉቀት አስተዳደር የልህቀት ማዕከል' በኮሌጁ ማቋቋምን በተመለከተ ግንቦት 24/2016 ዓም በኮሌጁ ዲን ጽ/ቤት መሰብሰብያ አዳራሽ ውይይት አካሂደዋል።

የኢትዮጵያ ደን ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሞቱማ ቶሌራ ሲናገሩ ኮሌጁ በሀገራችን በዘርፉ የሰዉ ኃይልን በማፍራት፣ በምርምር፣ በማማከር፣ እና በማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎቹ በርካታ ዓመታትን እንዳስቆጠረ አዉስተዉ ማዕከሉ በኮሌጁ መቋቋሙ እንደሀገር ቋሚ የሆነ የደን መረጃ አስተዳደርና አያያዝ የልህቀት ማዕከል እንዲሆን መመረጡ ይገባዋል ብለዋል::

የዚህ መሰሉ ማዕከል መቋቋም ዩኒቨርሲቲዉ ወደ ራስ ገዝ የምርምር ዩኒቨርሲቲነት ለሚያደርገዉ ጉዞ ጠቃሚ ግብዓት መሆኑን የጠቀሱት የዉጪ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ፅ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እመቤት በቀለ ዕቅዱን ተቋማዊ ለማድረግ ከዩኒቨርሲቲው የበላይ አመራር ጋር ተጨማሪ ዉይይት አድርጎ ወደ ውል ስምምነት መምጣት ይቻላል ብለዋል።

የኮሌጁ ዲን ተወካይ ዶ/ር በየነ ተክሉ ኮሌጁ የደን ልማት ዘርፍን ለማዘመን የሚረዳውን የልህቀት ማዕከል ማቋቋም እስካሁን ከነበረው አስተዋፅኦ የላቀ ጉልህ ሚና እንዲኖረው ያስችላል ካሉ በኃላ እስካሁን ያሉትንን ሃብቶች በመጠቀም ለተተኪዉ ትዉልድ እውቀቱን ለማስተላለፍ የሚችሉ የደን መረጃዉን በመሰብሰብ፣ በማደራጀትና በማስተዳደር ብቃት ያላቸው ከወጣት እስከ አንጋፋ ባለሙያዎች መኖራቸዉንም ገልፀዋል።

በዉይይቱም ማዕከሉ የደን መረጃን በማስተዳደር ደን ለሀገሪቱ ያለዉን ጠቀሜታ በማጎልበት ተጨባጭ መረጃ እንዲኖር በማስቻል ዘርፉን ለማሳደግ፣ ለውጭ የካርቦን ገበያ ዋጋ ግመታ ሁነኛ ተቋም እንዲሆን፣ ለተመራማሪዎችና ለፖሊሲ አዉጪዎች ግብዓትነት እንዲሁም ኮሌጁን የደን ትምህርትን ዲጅታይዝ አድርጎ ዲጂታል ካምፓስ ለማድረግ የማዕከሉ መቋቋም አስፈላጊነት፣ እንዴት እንደሚቋቋም፣ በቀጣይ ምን ስራዎች መሰራት እንዳለባቸዉ፣ ቀደምት ከነበሩ ፕሮጀክቶች ምን ትምህርትና ግብዓት እንደተገኘ፣ የሚሉት ነጥቦች ላይ እንዲሁም የማዕከሉን ምስረታ ዓላማና ቀጣይነት ላይ መነሻ ፅሁፍ ከCIFOR-ICRAF በመጡት ዶ/ር ሃብተማርያም ካሳ ቀርቦ ዉይይት ተካሂዷል::

በመጨረሻም በአጭር ጊዜ ኮሌጁ የመግባቢያ ሰነዱን የሚያጎልበቱ ቴክኒካል ቡድን እንዲያቋቁምና የመግባቢያ ሰነድን በመፈራረም ወደስራ እንዲገባ የኮሌጁ አመራሮች: ምሁራን እና የደን ልማት የጋራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et