የዲዛይን ውድድር የሽልማት ሥነ ስርዓት ተካሄደ

የኪነ ህንጻ ት/ክፍል ተማሪዎች የዲዛይን ውድድር የማጠቃለያ ሽልማት ሥነ ስርዓት ተካሄደ::

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኪነ-ህንጻ ተማሪዎች ላለፉት ሶስት ወራት ሲሰሩት የነበረው ‘Eco Lodge’ የዲዛይን ውድደር ልምድ ባላቸው አርክቴክቶች  ተገምግሞ ለማጠቃለያ ሽልማት በቅቷል። 

ተማሪዎቹ በተለያየ ቡድን በመዋቀር በሐልዮት የተማሩትን ወደ ተግባር በመቀየር፣ ያገኙትን ዕድል ተጠቅመው የሰሩት አርክቴክቸራል ዲዛየን ለሽልማት እንዳበቃቸው በርክክብ  ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው በንግግር የጀመሩት የት/ክፍሉ ሀላፊ አቶ ኮኖ ቦዴ ተናግረዋል። "ይህ ዕድል መምጣቱ እንደበጎ የሚወሰድና፣ በተቋሙና በኢንቨስትመንቱ መካከል የሚገነባውን ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ አድርሶ፣ ተቋሙ በክፍል ከሚሰጠው የመማር ማስተማር ሂደት በተጨማሪ፣ በአገር የተያዙ የልማት ዕቅዶችን ለማገዝ ትልቅ ሚና ለመወጣት እንደሚያስችል ማሳያ ነው፤" ሲሉ ገለፀዋል።

የቴ/ኢንስትቲዩት  የምርምርና ቴክ/ሽግ/ም/ዳይሬክተር ዶ/ር ገብረክርስቶስ ኑርዬ "እንደዚህ ዓይነት እድሎች ሲመጡ፣ የተማሪዎችን የብቃት ደረጃ በተግባር የተፈተሸ ልህቀት የሚያጎናፅፍ ከመሆኑም በላይ የመወዳደር፣ የሙያ ማዳበር፣ የስራ ፈጠራና፣ የጊዜ አጠቃቀምን ጭምር ያስተምራል፤" ብለዋል።

በተሳትፎ ያገኙት ልምምድ ለተማሪዎቹ ጥሩ መሰረት የጣለላቸውና ለወደፊቱ የሙያ ብቃት ማዳበሪያ ስለመሆኑ የተናገሩት ወጣቱ ባለሀብትና 'የጆምቦላ ኢኮ ሎጅና ስፓ' ባለቤት አቶ በረከት ክፍሌ፣ "ይህንን የኢንቨስትመንት ስራ ፕሮጀክት በማመን ለተቋሙ ተማሪዎችና መምህራን መሰጠቱ የሚበረታታ፣ የሚያስመሰግንና ወደፊት በጋራ ለሚሰሩ ስራዎች ጥሩ ድልድይ ነው፤" ሲሉ ተናግረዋል።

ስራውን በማስተባበር፣ በመገምገምና የውድድር መስፈርቶችን በማቀናጀት ሀላፊነታቸውን ለተወጡት መምህራን የምስጋና መድረክ፣ ለተሳታፊ ተማሪዎች ደግሞ የዕውቅና የምስክር ወረቀት፣ በፕሮጀክቱ ዲዛየን ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡት የኪነ ህንጻ ት/ክፍል ተማሪዎች  የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማትና እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et