አስደሳች ዜና

ግንቦት 5/2016 ዓም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት አምስት አመታት በጤና መረጃ ስርዓት ላይ በሠራው ሥራ የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር የላቀ አፈፃፀም ተሸላሚ ሆኗል።

የሽልማቱ ስነስርዓት በዛሬው ዕለት በስካይ ላይት ሆቴል በተደረገው የጤና መረጃ ሳምንት አጀማመር ፕሮግራም ላይ ሲሆን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክዘኩዩቲቭ ዳይሬክተር አለሙ ጣሚሶ (ተባ. ፕሮፌሰር) ከጤና ሚንስትር ደኤታው ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እጅ ተቀብለዋል::

የጤና መረጃ ሥርዓት ላይ የተሰራው ሥራ እንደሀገር ከጤና ሚንስቴር አምስቱ ስትራቴጂክ ዕቅድ የትኩረት ዘርፎች አንዱ ሲሆን ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሀገር ደረጃ ሞዴል ከሆኑት ሰባት ወረዳዎች ሁለቱን ማለትም ከሲዳማ ክልል የሸበዲኖ እና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳንኩራ ወረዳዎችን ሞዴል በማድረግ በሠራው ሥራ እና አዳዲስ ምርምሮችን በመሥራት የላቀ አፈፃፀምና የልዩ አፈፃፀም ሽልማት አግኝቷል::

እንኳን ደስ አለን!

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et