ሀዩ የከተሞች ፎረም ላይ እየተሳተፈ ይገኛል

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ9ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከየካቲት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ባለው ዘጠነኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ላይ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ልዑካን ጋር ሆኖ እየተሳተፈ ይገኛል::

"የዘመኑ ከተሞች ለኢትዮጵያ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው በዚሁ መድረክ ላይ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከተመሰረተበት ግዜ ጀምሮ የትምህርት ዕድልን ለአካባቢው ማህበረሰብ በማስፋፋት: ችግር ፈች የምርምር ስራዎችን በመስራት: በጤናው ዘርፍ ዘመናዊነትና ሰፊ አገልግሎት በማቅረብ ላይ ላቅ ያለ ሚና በመጫወት: ለወጣቶችና ሴቶች እንዲሁም በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የስራ ዕድል በመፍጠር: የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ በማድረግ እና የአቅም ግንባታ ሥራን በመስራት ለሀዋሳ ከተማ እንዲሁም ሌሎች በአቅራቢያው የሚገኙ ከተሞች ዕድገት እና ዘመናዊነት በተለያየ መልኩ ለዓመታት ሲያበረክት የቆየው እና እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ ለጎብኝዎች እይታ ቀርቧል:: ለእይታ ከቀረቡ ሥራዎች መካከል የከተማ ግብርና: የአረንግዋዴ ልማት: በምርምር-ተኮር የአካባቢ ጥበቃ: የታዳሽ ኃይል ቴክኖሎጂ ተደራሽነት: የህንፃዎች እና ምድረግቢ ውበት ተዋፅኦዎች እንዲሁም ዓለም አቀፍ ደረጃ ያሟላ ስታድየም ባለቤት መሆኑ የሚጠቀሱ ናቸው::

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et