የ2015 በጀት ዓመት አፈፃፀምና የ2016 ዕቅድ ግምገማ መድረክ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2016 መሪ ዕቅድ የግምገማ መድረክ ለሁለተኛ ቀን በወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ቀጥሎ ውሏል::

በዕለቱም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የስራ ክህሎት ማጎልበቻና ስነ መቀጠር ማዕከል ኃላፊ አቶ ክብረት ፍቃዱ በ2015 በጀት ዓመት የዩኒቨርሲቲው ምሩቃንን ለማብቃት በማዕከሉ የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት እንዲሁም የቀድሞ የዩኒቨርሲቲያችን ምሩቃንን የመቀጠር ወይም ሥራ የመፍጠር ሁኔታ በተመለከተ የተሰራውን የዳሰሳ ጥናት ውጤት አቅርበዋል::

በማስከተልም የጥራት ማረጋገጫና ማሻሻያ ዳይሬክተሯ ዶ/ር አቻምየለሽ ገ/ፃዲቅ ባለቀው የበጀት ዓመት የተሰራውን የአካዳሚክና የአስተዳደር ሥራዎች የጥራት ደረጃ አስመልክቶ የተደረገ መሰረታዊ የዳሰሳ ጥናት ውጤት ለውይይትና ግብረመልስ ያቀረቡ ሲሆን የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲን የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ መሰረት አድርጎ የተዘጋጀው የመጪው 2016 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ በፕላንና ተቋማዊ ለውጥ ዳይሬክተሩ አቶ ሙሉጌታ ቡርቃ ለውይይትና የማሻሻያ ሃሳቦች ቀርቧል::

የጉባኤው ተሳታፊዎችም በቀረቡት ሁሉን አቀፍ አርዕስት ላይ ዝርዝር ገብረ መልሶችን የሰጡ ሲሆን በቀጣይ ሊሰራባቸው የሚገባ ጉዳዮች ላይ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር አያኖ በኩል ቀጣይ አቅጣጫና የስራ መመሪያ ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠናቋል::

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et