ማስታወቂያ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም  አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች  እንዲሁም በ2015 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርት ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ነባር የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ  ጊዜ ታህሳስ 08-09/2016 . መሆኑን ይገልጻል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦

  • የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ
  • የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

ማሳሰቢያ

 ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጡ የሚከተሉትን ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡

  • የ12ኛ ክፍል ፈተና ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
  • ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
  • አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
  • አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
  • የስፖርት ትጥቅ
  • ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡

     

 የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ  ሬጅስትራር እና አልሙኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et