ማስታወቂያ

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ እንኳን ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አደረሳችሁ እያለ የመደበኛ እና የተከታታይና ፕሮግራም ተማሪዎች የ2015 ዓ.ም ምዝገባ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ቀናት በሁሉም ካምፓሶች የሚከናወን መሆኑና ያሳውቃል።

ሀ. ለሁለተኛ ዲግሪ እና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች

  1. ሁለተኛ ዓመትና ከዚም በላይ ለሆኑ መደበኛ እና የእረፍት ቀናት የድህረምረቃ (ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ) ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ ጥቅምት 21-22/2015 ዓ.ም፡፡
  2. ለአዲስ ገቢ አንደኛ ዓመት መደበኛ እና የእረፍት ቀናት የድህረምረቃ (ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ) ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ ጥቅምት 23-24/2015 ዓ.ም፡፡

ለ. ለመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች

  1. የማታና የእረፍት ቀናት የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ ጥቅምት 25-27/2015 ዓ.ም
  2. ነባር የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ ጥቅምት 28-29/ 2015 ዓ.ም

ሳሰብያ፡-

  • የአንደኛ ዓመት መደበኛ (Freshman) ፕሮግራም ተማሪዎች ሆናችሁ በመልሶ ቅበላ መግባት የምትችሉ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ከ2015 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጋር መሆኑን እናሳውቃለን።
  • ከተጠቀሰው ቀን አስቀድሞ አሊያም ዘግይቶ የሚመጣ ተመዝጋቢን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን።

 ሬጅስትራርና አልሙኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et