የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ በበየነ መረብ ”Online” ከግንቦት 01-05/2014 ዓ.ም ድረስ የሚከናወን ሲሆን የተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ የመግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ግንቦት 08-09/2014 ዓ.ም በዋናው ግቢ መሆኑን ይገልጻል፡፡
ማሳሰቢያ፦
- ስለምዝገባ ሂደቱ ዝርዝር ማመልከቻውን ሂደት ቅደም ተከተል ለማውረድ ይህንን ይጫኑ
- ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጡ የሚከተሉትን ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡
1ኛ. የ12ኛ ና 10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ቅጂው
2ኛ. ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክርቢት ዋናውና ቅጂው
3ኛ. የሌሊት አልባሳት
4ኛ. አራት (4) ጉርድ ፎቶ ግራፍ
5ኛ. የስፖርት ትጥቅ
- በተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2014 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ግንቦት 10 እና 11 2014 ዓ.ም እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡
- ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡
ተማሪዎች ዩኒቨርስቲ ሪፖርት የማድረጊያ ጊዜ ግንቦት 08-09/2014 ዓ.ም ሲሆን
1. በ Natural Science and Teacher Education in Natural Science የተመደባችሁ በዋናው ግቢ
2. በ Social Sciences Teacher Education in Social Science የተመደባችሁ በቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት(IOT) መሆኑን እናሳውቃለን።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር እና አልሙኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት