የሙያ ብቃት ማሻሻያ ስልጠና መስጠት ተጀመረ

ለከተማ መሬትና ፕላን ዘርፍ ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ማሻሻያ ስልጠና ተጀመረ::

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር በመተባበተር ከሲዳማ፡ ደቡብ: ማእከላዊ ኢትዮጲያ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ክልሎች ለተወጣጡ 100 የከተማ መሬትና ፕላን ዘርፍ ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ማሻሻያና መመዘኛ ስልጠና የማስጀመሪያ መርሃግብር ሚያዚያ 7/2016 ዓም ተከናውኗል::

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር አያኖ በራሶ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በከፍተኛ ትምህረት ተቋማትና ሴክተር መስሪያ ቤቶች መካከል ጠንካራና ትረጉም ያለዉ ግንኙነት መፍጠር አዳዲስ ሀሳቦችንና ቴከኖሎጂዎችን ለማፈለቅ የጎላ ሚና እንዳለዉና በተለይም ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸዉን የተማረ የሰዉ ሀይል፡ የምርመር ማእከላት፤ ዎርክሾፖችና ላብራቶሪዎቸን ጥቅም ላይ በማዋል ከሴክተር መሰሪያ ቤቶች ጋር ቢቀናጁ ወጪ ቆጣቢ በሆነ ሁኔታ ሀገሪቱን ብሎም ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎችን ማከናዎን እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ ፕሬዚደንቱ እንዳሉት በዚህ ረገድ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከበረካታ ተቋማት ጋር በርካታ ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ትብብሮችንና ስምምነቶችን በመመስረት በሰፊዉ እየተነቀሳቀሰ መሆኑንና ይህ ከኢ.ፌ.ድ.ሪ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር በመታባበር የተዘጋጀዉ ስልጠናም አንዱ ማሳያ ነው፡:

የእለቱ የክብር እንግዳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ መሬት ሀገሪቱ ካላት ዉስን ሀበት አንዱና ዋነኛዉ በመሆኑ በሰለጠነ መንገድ ይመራ ዘንድ ሁሉም ባለድረሻ አካል በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጎላ ሚና መጫወት አንዳለባቸዉ አሳስበዉ ይህ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ወንዶ ገነት ደ/ተ/ሃ/ኮሌጅ ለከተማ መሬትና ፕላን ዘርፍ ባለሙያዎች ለ 45 ቀናት የሚሰጠዉ ስልጠናም ይህንን ታሳቢ ተደረጎ የሚሰጥ የክህሎትና የሙያ ማጎለበቻ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በ45 ቀናት ውስጥ የሚሰጠውን ስልጠና የሚወስዱት ከአራቱ ክልሎች የተውጣጡ 100 ባለሙያዎች ስልጠናውን ካጠናቀቁ በኃላ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና የሚወስዱ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ከስልጠና ማስጀመሪያ መርሃግብሩ በኃላ ተጋባዥ እንግዶች በኮሌጁ እየተሰሩ ያሉ የምርምርና ልማት ሥራዎችን ተጎብኝተዋል::

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et