መስከረም 9/2017 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ በተካሄደው የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የኮከቦች ሽልማትና የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሦስት ሚልዮን ብር ሽልማት ተበርክቶለታል::
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክስዮን ማህበር ለመሸለም የበቃው የሊጉን የመጨረሻ ጨዋታ ጨምሮ 64 ጨዋታዎችን በዋናው ግቢ ባስገነባው አለማቀፍ ስታዲየም እንዲካሄድ በመፍቀድ በእግር ኳስ ስፖርት እድገት ላይ የራሱን አስተዋፅኦ በማድረጉ ነው::
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በስፖርት ሳይንስ ዘርፍ ብቁና አለማቀፍ ተወዳዳሪ የሆኑ ባለሙያዎችን ለማፍራት እንዲረዳው ያስገነባው ስታዲየም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ሀዋሳ ከተማ ላይ እንዲደረጉ በማስቻል ለተከታታይ ዓመታት የራሱን አሻራ አኑሯል::