የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2012ዓ.ም ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምሪፖርት ውይይት አደረገ

HalfYear-report-01

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ በዋናው ግቢ ከጥር 29/2012 ጀምሮ ለሁለት ቀናት ግምገማና ውይይት አደረገ፡፡

ዶ/ር አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በመክፈቻ ንግግራቸው ዩኒቨርሲቲው እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ በዚህ ዓመትም ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማር፣ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎት ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን ገልጸው በሃገሪቱ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከሚፈጠሩ አለመግባባቶች ጋር ተያይዞ በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥም የሰላምና ጸጥታ ችግሮች በመኖራቸው የመማር ማስተማሩ ሂደት እየተቆራረጠና እየተስተጓጎለ ሲሆን በዩኒቨርሲቲያችን ግን በተቻለ መጠን ይህ ችግር እንዳይፈጠር በመሥራታችን የመጀመሪያው ሴሚስተርን በሰላም ያጠናቀቅን በመሆኑ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ሊመሰገን ይገባዋል ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አክለውም በዛሬው የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ግምገማና ውይይት በማድረግና ድክመቶቻችንን በማረም በቀጣይ ሁላችንም የተጣለብንን ኃላፊነት በመወጣት የተሻለ ሥራ መሥራት ይኖርብናል በማለት አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ውይይት ተደርጎ አስተያየት ተሰጠባቸው ሲሆን ጠንካራና ደካማ ጎኖችንም በመለየት ቀጣይ አቅጣጫዎችንም በማሰቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

      በስለሺ ነጋሽ

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.