የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያንቺ ንቅናቄ ( Yanchi movement ) ለሶስት ቀን በሚቆየው የሴት ልጅ ጥቃትን በመቃወም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅተዋል

Yanchi

"አልፈልግም ማለት አልፈልግም ነው!"

• "አቁም" ማለት አልፈልግም ነው!

• "መሸሽ" ማለት አልፈልግም ነው!

• "እምቢ" ማለት አልፈልግም ነው!

• "መግፋት/መገፍተር" ማለት አልፈልግም ነው!

• "ዝግጁ አይደለሁም" ማለት አልፈልግም ነው!

• "ተወኝ" ማለት አልፈልግም ነው!

• "ዞር በል" ማለት አልፈልግም ነው!

• "መጮህ" ማለት አልፈልግም ነው!

• "እረፍ" ማለት አልፈልግም ነው!

• "ማልቀስ" ማለት አልፈልግም ነው!

የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያንቺ ንቅናቄ ( Yanchi movement ) ለሶስት ቀን በሚቆየው የሴት ልጅ ጥቃትን በመቃወም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅተዋል፡፡ ዝግጅቱ ትላንት የተጀመረ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው 16 ቀን ንቅናቄ አንድ አካል እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸውልናል፡፡ በዚህ ንቅናቄ በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ ሌሎች ክበባትም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በሌላ በኩል በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው "መራሂት ክበብ" አትኩሮቱን ሴት ተማሪዎችን በማብቃት ላይ አድርጎ እየሰራ ሲሆን ለሴት ተማሪዎች የፅዳት መጠበቂያ የሚሆን 88 ካርቶን ሞዴስ በመግዛት ለሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሴቶች ህፃናት ወጣቶች እና ኤችአይቪ ኤድስ ዳይሬክትቶሬት አስረክበዋል። የመጀመሪያውን ድጋፋቸውንም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቅርንጫፍ በሆነው በአዋዳ ካምፓስ አድርገዋል።

ተማሪዎቻችን እየሰራችሁት ላለው መልካም ስራና ለሌሎች ወጣቶች ትምህርት የሚሰጥ ተግባር ላይ በመሳተፋችሁ ያለንን ምስጋና እናቀርባለን!

#HawassaUniversity

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.