ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በጤና ልማት ዘርፍ ሀገራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ እንደሆነ ተገለፀ

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በጤና ልማት ዘርፍ የተጣለበትን ማህበራዊና አገራዊ ሀላፊነት እየተወጣ እንደሆነ ተገለፀ፡፡ ይህ የተገለፀው የዩኒቨርስቲው ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና ትምህርታቸውን የተከታተሉ 14ዐ የህክምና ዶክተሮችን ባስመረቀበት የምርቃ ስነስርዓት ላይ ነው፡፡

በምረቃው ስነስረዓት የክብር እንግዳ የነበሩት የጤና ሚኒስተር ሚኒስተር ዴኤታ ወ/ሮ ሰአሀርላ አብዱላሂ እንደገለፁት ኢትዮጵያ ያለፉት ሀያ እና ሰላሳ አመታት በሌሎች ሴክተሮች እንደታየው ሁሉ በጤናው ዘርፍም ከፍተኛ የሆነ እና በአለም ጤና ድርጅት ጭምር እውቅና የተሰጣቸው ስኬቶች ብታስመዘግበም አሆንም ቢሆን የህብረተሰቡን የጤና ሸፋን በመጨመርና ጥራትና ፍጥነት ያለው የጤና አገልግሎት ከመስጠት አንጻር ብዙ እንደሚቀር ገልፀው ይህን ክፍተት ለመሙላት ሚኒስተር መስሪያቤታቸው ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ተጨባጭ ለውጥ በማምጣት እየሰራ መሆኑንና የሀዋሳ ዩንቨርስቲ በሀገሪቱ ከሚገኙ የስልጠና ማእከሎች በቁጥርም በጥራትም በተሻለ የስልጠና መዓከል በመክፈት ብቁባለሙያዎች በማፍራትና የጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ የሚኒስቴር መስሪያቤቱ አላማ እየደገፈና የተጣለበትን አገራዊ ሀላፊነት እየተወጣ በመሆኑ የላቀና ከፍተኛ ምስጋና እንደተቸረው ገልፀዋል፡፡

የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስክዩቲቭ ዶ/ር አቤል ገደፋው በእለቱ እንደገለፁት ኮሌጅ ስራውን ከ1995 ጀምሮ በህክምናው ዘርፍ የተጣለበትን ብቁ የህክምና ባለሙያዎች የማፍራት ሀላፊነት ከግብ ለማድረስ ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን ገልፀው በዚህም ረገድ ከ2ዐዐ1-2ዐ11 ባሉት አመታት በሺዎች የሚቆጠሩ የህክምና ዶክተሮችና ባለሙያዎችን በማስመረቅ የሚጠቀምበትን ማህበራዊና አገራዊ ሀላፊነት እየተወጣ እንደሆነ ተናግርዋል፡፡

የትምህርት ጥራት ከማሻሻል ረገድም የህክምና ትምህርት ጥራት ለማሻሻል በከፍተኛ ትምህርት ጥራት አግባበብነት ባለስልጣንና አጋር ድርጅቶች የተዘጋጀውን የህክምና ትምህርት የጥራት ደረጃ መስፈርት ለማሟላትና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን ህክምና ትምህርት ቤቱ በከፍተኛ ሀላፊነት እየሰራበት ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥም ቀሪስራዎችን በማጠናቀቅ የመስፈርት ጥያቄው ለሚመለከተው አካል አንደሚቀርብ ዶ/ር አቤል ገልፀዋል፡፡

የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት አቶ አያኖ በራሶ ባስተላለፉት መልክት ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙት 1ዐ ምርጥ ዩኒቨርስቲዎች አንዱ የመሆን ራይ አንግቦ በመስራት ላይ አንደሚገኝ ጠቅሰው በአገሪቱ ፍላጐት ላይ በመመስረትም የተለያዩ የትምህርት ፣ሮግራሞችን ቀርጾ በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ መርሀ ግብሮች ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሀይል በማፍራት አገሪቱ የወጠነችውን ሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልጸው በዚህም ረገድ የዩኒቨርስቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዘርፉ ያለውን የባለሙያ እጥረት በመቅረፍ እና ተፈላጊና ብቁ የጤና ባለሙያ በማፍራት በክልሉም ሆነ በሀገር ደረጃ በጤናው ልማት ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጾ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.