የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ካሰኬፕና የተቀናጀ የዘር ዘርፍ ልማት ዩኒት ፕሮጀክቶች ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሄዱ፡፡

 የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ካሰኬፕና የተቀናጀ የዘር ዘርፍ ልማት ዩኒት ፕሮጀክቶች በብቅል ገብስ ምርትና የገበያ ትስስር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሄዱ፡፡

ፕሮፌሰር አለማየሁ ረጋሳ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት በመክፈቻ ንግግራቸው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሶስት ዋና ዋና ተልዕኮዎች ማለትም ማስተማር|ችግር ፈቺ ምርምር ማካሄድ እና ማህበረሰብ አገልግሎት ማከናወን ሲሆን በአሁኑ ወቅት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 57 የትብብር ፕሮጀክቶች ከ 174 አለም አቀፍ እና ከ84 ሀገር በቀል ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ በመሆኑ ካሰኬፕና የተቀናጀ የዘር ዘርፍ ልማት ዩኒት ፕሮጀክቶችም የዚሁ ትብብር አካል መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ፕሮፌሰር አለማየሁ አክለውም ካሰኬፕና የተቀናጀ የዘር ዘርፍ ልማት ዩኒት ፕሮጀክቶች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ከሰሩባቸው ዘርፈ ብዙ የግብርና ምርምር ተግባራት መካከል የብቅል ገብስ ሰብል በክልሉ አንድ ኮሞዲቲ ሆኖ እንዲወጣ ያስቻለ ሲሆን በዚህ የውይይት መድረክ የብቅል ገብስ እዚት ሰንሰለት በማጠናከር ወደ ሀገር ቤት የብቅል ገብስ በማስገባት የሚወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ መቀነስና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት በማሳደግ ኑሮውን ማሻሻል ላይ ትኩረት ሰተን መወያየት ይኖርብናል በማለት ፕሮግራሙ መከፈቱን አብስረዋል፡፡

አቶ አበራ መኮንን በኦሮሚያ ክልል ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌደሬሽን የአሰላ ብቅል ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ እንደገለጹት ፋብሪካው ብቅል ከፈረንሳይ እና ቤልጀም በርካታ የውጭ ምንዛሪ በማውጣት የሚያስመጣ ሲሆን በሀገር ውስጥ መመረት መጀመሩ እንደ ሃገርም የውጭ ምንዛሪን ያስቀርልናልና በቀጣይም ተጠናክሮ መሰራት አለበት ብለዋል፡፡

በዕለቱም በተመራማሪዎች ጥናቶች የቀረቡ ሲሆን ከባለድርሻ አካላትም ጠቃሚ ሀሳቦች ተነስተው ወይይቱ የተሳካ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

 በስለሺ ነጋሽ

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.