የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮምሽን የነጭ ሪቫን ቀንን አስመልክቶ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምክክር መድረክ አዘጋጀ፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮምሽን ቢሮ ሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት " ጀግኒት ወንድ ልጇን ለሰብዓዊ መብቶች በማስተማር ጾታዊ ጥቃትን ትከለክላለች" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን የጸረ ጾታዊ ጥቃት ዘመቻ (የነጭ ሪቫን ቀን) ምክንያት በማድረግ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ ተማሪዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡

HU010592

አቶ አየለ አደቶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ በዛሬው ለት የምናደርገው የምክክር መድረክ ለቀጣይ ትውልድ መሰረት የሚጥል ሲሆን ተማሪዎቻችን ከተለያዩ ቦታዎች ከቤተሰቦቻተው ተለይተው ስለሚመጡ ለተለያጡ ችግሮች ሲጋለጡ በመስተዋሉ ይሄንን ለመከላከል እና አምራች ዜጋን ለመፍጠር የሁላችንም ድርሻ በመሆኑ እኛ ተረድተን የሌሎችንም እውቀት በሰብዓዊ መብትና ጾታዊ ጥቃት ላይ የግንዛቤ ስራዎችን ልንሰራ ይገባል ብለዋል ፡፡

ወ/ሮ ቤተልሄም ታደሰ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮምሽን ቢሮ ሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሴቶችና ህጻናት ዳይሬክተር ጾታዊ ጥቃት ተያያዥ በመሆኑ ለተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣የአካል መጉደል፣የስነ ልቦና ቀውስ እና ከሰው ጋር ቀርቦ የመግባባት ችግር ያጋጥማልና በዚህ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሰራት ያለባቸው ሲሆን ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መከላከል ላይ ኮምሽኑ ብቻ ሳይሆን ዩኒቨርሲቲው፣ ምሁራኑ እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም አብሮ መስራት ይኖርበታል ካሉ በኃላ ተማሪዎችም እራሳቸውን ለመጡለት አላማ መስጠት ይኖርባቸዋል በማለት አሳስበዋል፡፡

በዕለቱም የተለያዩ ጥናቶች የቀረቡ ሲሆን በተሳታፊዎችም ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

 

በስለሺ ነጋሽ

 

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.