ሀዋሳ ዩኒቨረሲቲ በምርምር የተገኙ የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶአደሩ ተደራሽ እያደረገ መሆኑ ተገለጸ

ሀዋሳ ዩነቨርሲቲ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸዉን እና በሳይንሳዊ ምርምር በልህቀት የተገኙ የሰብል ዝርያዎችን ወደ አርሶ አደሩ በማስፋት ተደራሽ እያደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው በዩነቨርሲቲው ምርምር ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ድጋፍ በሁላና አርቤጎና ወረዳዎች ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን የትሪትካሌ ሰብል ዝርያዎች ምረታማነት ጥናት ዙሪያ የመስክ ጉበኘትና ግምገማ ፕሮግራም ላይ ነው፡፤

HU010759

በፕሮግራሙ ላ ይ የተገኙት የሀዋሳ ዩንቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትልፕሬዚደንት ፕሮፌሰር አለማየሁ ረጋሳ ዩኒቨርሲቲዉ ከመደበኛዉ የመማር ማስተማር ስራ ጎን ለጎን ማህበረሰቡን እና አርሶአደሩን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን ቀረጾ ሳይንሳዊ መርምር በማካሄድ በልቀት የተገኙና ምርታማነታቸዉ የተረጋገጠ የምርምር ዉጤቶችን በማስፋት ለአረሶአደሩ ተደራሽ እንደሚያደርግ ጠቅሰዉ ይህ በሲዳማ ዞን ሶስት ወረዳዎች ተግባራዊ እየተደረገ ያለዉ የትረተካል ሰብል ዝርያዎች ምርታማነት ጥናትና የማስፋፋት ስራ ዩነቨርሲቲዉ ከሚተገብራቸዉ ፕሮጀክቶች አንዱ ማሆኑን ተናገረዋል፡፡

የፕሮጀክቱን እንቅስቃሴ አሰመልክቶ ገለጻ ያደረጉት በሃዋሳ ዩነቨርሲቲ ግበርና ኮሌጅ የሰበል ተመራማሪ እና የፕሮጀከቱ ኣስተባባሪ ዶክተር ደመላሽ ከፈለ እንደገለጹት የትርተካሌ ምርምር በአገራችን የስንዴና ቦቆሎ ዝርያዎች ማሻሻያ ፕሮጀክት ከብሄራዊ ምርምር ተቁአማት ጋር በመተባበር በ1970 እንደተጀመረና አላማዉም የተረትካሌ ዝርያዎችን በማላመድና የምርታማነት ጥናት በማካሄድ የላቀ ምርታማነት ያላቸዉን ዝርያዎች የአመራረት ዘዴ ጥምርታን በማረጋገጥ ለአርሶ አደሩ ማስተዋወቅና ተደራሽ ማድረግ ነዉ፡፡ ይህንንም መሰረት በማድረግ የተቀናጀ የትርትካሌ ፐሮጀክት በዩኒቨረሲቲዉ መርምር ፐሮገራም ዳይሬክቶሬት ድጋፍ ታቅዶ ከ2017 ጀምሮ በደቡብ ኢትዮጲያ የተለያዩ ወረዳዎቸ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ዶክተር ደመላሽ ገልጸዉ በሲዳማ ዞን በሚገኙ ሁላ፡ አረቤጎና እና ወነዶገነት ወረዳዎች በዩኒቨረሲቲዉ ተግባራዊ እየተደረገ ያለዉ ፐሮጀክተም የዚህ አነዱ አካል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዶክተር ደመላሽ አክለዉ እነደተናገሩት አከባቢዉን በላቀ ሁኔታ የተላመዱና ከፍተኛ ዉጤት ያስገኙ ሁለት የተርትክሌ ዝርያዎች ማለተም ዘንካቴ አና ደረሰልኝ በሁላና አረቤጎና ወረዳዎች በ20 አረሶ አደሮች ማሳ ላይ የማጠቃለያ ጥናት እየተካሄደ ሲሆን የዩንቨርሲቲዉ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬከቶሬት በቀታይ ግዜ የምርምሩን ዉጤት የማስተዋወቅና የማሸጋገር ስራ እንደሚያከናዉን ገልጸዋል፡፡

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.