የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በካንጋሮ እናት እንክብካቤ ዙሪያ ምክክር አካሄደ

HU011080

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በካንጋሮ እናት እንክብካቤ(Kangaroo Mother Care) በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር አውደርዕይ በወንዶ ገነት የደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ አካሄደ፡፡

ዶ/ር መሳይ ሀይሉ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአ/ሰ/ም/ፕሬዚዳንት ዩኒቨርሲቲው ባለፉት አመታት ከአንጋፋና ቀዳሚ ከሆኑት ዩኒቨርሲቲዎች ተወዳድሮ ከ1ኛ-3ኛ በመውጣት ውጤታማ መሆኑን በመማር ማስተማር፣ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ያስመሰከረና እየሰራ ያለ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ዘንድሮ በከፈተው 7ኛ የበንሳ ዳዬ ካንፓስን ጨምሮ ከ48000 ተማሪዎች በላይ በቀንና በማታ ተቀብሎ እያስተማረ መሆኑን ገልጸው ዩኒቨርሲቲው ከ200 በላይ አለም አቀፍ ተማሪዎችን የተቀበለና ከ70 በላይ አለም አቀፍ ምሁራን የሚገኙበት እንዲሁም ወደ 55 የሚደርሱ አለም አቀፍ ፕሮጀክቶች ከተለያዩ ሀገራት ጋር በትብብር እየሰራን በመሆኑ የዛሬውም የካንጋሮ እናት እንክብካቤ ውጤታማ ከሆኑት አንዱ ነው በማለት ፕሮጀክቱ ውጤታማ እንዲሆን ለሰሩ ዩኒቨርሲቲው ምሁራንና ባለድርሻ አካላትን አመስግነው ፕሮግራሙን ከፍተዋል፡፡

ዶ/ር ሄኖክ ታደለ (ተ/ፕሮፌሰር) በሪፈራል ሆስፒታል የህጻናት ስፔሻሊስት በአለም ላይ ከሚወለዱ ህጻናት 15 ሚሊዮን የሚሆኑት ከክብደት በታች ሆነው የሚወለዱ ሲሆን በ2016 እ.አ.አ በተሰራ ጥናት በአመት በአለም ላይ የጨቅላ ህጻናት ሞት 2.6 ሚሊዮን እንደተመዘገበ ገልጸው ይሄንን ለመቀነስ በምርምር ከተገኙ መፍትሄዎች የካንጋሮ እናት እንክብካቤ አንዱ በመሆኑ እኛም ይሄንኑ የምርምር ፕሮግራም ከአለም ጤና ድርጅት ጋር ቀርጸን ከሶስት አመት በፊት በዩኒቨርሲቲው ሪፈራል ሆስፒታል የጀመርን ሲሆን ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋርም በመተባበር በሌሎች ሶስት ሆስፒታሎችም አገልግሎቱ እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል፡፡

ዶ/ር ሄኖክ አክለውም የካንጋሮ እናት እንክብካቤ በደረት ላይ ልጆችን በማድረግ የቆዳ ለቆዳ ንክኪ ሲሆን ጡት ማጥባትና የቤተሰብ እገዛና ድጋፍ ተያያዥ አገልግሎት መሆናቸውን ገልጸው በዚህም የልጆቹ አተነፋፈስ ስርዓት ይስተካከላል፣በቂ ሙቀት ያገኛሉ፣ለትህዋስያን እንዳይጋለጡ ይረዳል ፣ የሆስፒታል ቆይታን ይቀንሳል፣ሞትን ይቀንሳል እንዲሁም የእናትና ልጅ ፍቅርንም ይጨምራል ብለዋል፡፡

 

       

 

በስለሺ ነጋሽ

 

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.