በዩኒቨርሲቲው ሴት ተማሪዎችን ማብቃት ትኩረት ተሰቶታል

 MG 8603

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የዩኒቭርሲቲው ስርዓተ ፆታ ና ኤች አይቪ /ኤድስ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቴር ሲ/ር ትዕግስት ከበደ ገለፁ፡፡  በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ወደ ዩኒቨርሲቲው ለመጡ አዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች የምክክር መድረክ ላይ እንዳስታወቁት ዩኒቨርሲቲው ሴት ተማሪዎችን ለማብቃትና ተሳትፎአቸውንና ተጠቃሚነታቸውን በሁሉም መልክ ለመጨመር ዘርፈብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በዚህም መሰረት በዩኒቨርሲቲው ስር በሚገኙ 7ቱም ካምፓሶች የስርዓተ-ፆታና ኤች አይ ቪ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች መደራጀታቸውንና ሴት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው ለሚገጥማቸው ማናቸውም ችግሮች ከጎን ሆኖ ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስረድተዋል፡፡

ከሚመጡበት አከባቢ የድኀነት ድጋፍ ማስረጃ ይዘው ለሚመጡና ተጨማ ድጋፊ ለሚያስፈልጋቸው ሴት ተማሪዎች ከተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ከዩኒቨርሲው ለዚሁ በተሰጠው የገቢ ማመንጫ ፕሮጀክት በሚገኘው ገንዘብ አስፈላግ የሆኑ የንጽህና መጠበቂያና የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡ 

ኀዳር 09/2011 ዓም በዋናው ግቢ የአፍሪካ ኀብረት አደራሽ በተካሄደው በዚሁ ፕሮግራም ላይ ከሁሉም ካምፓሶች የተውጣጡ ከ1000 (አንድ ሺ) በላይ ሴት ተማሪዎች መሳተፋቸው ታውቋል፡፡

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.