የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የማስፈጸም አቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ

 

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የፕላንና ተቋማዊ ለውጥ ዳይሬክቶሬት የአመራሩን እውቀትና ክህሎት በማሳደግ የቁልፍና አበይት ተግባራትን ለማሻሻል የሚያስችሉ በBSC ዕቅድና ምዘና ስርዓት፣ የዜጐች ቻርተር፣የስብሰባ መመሪያ እና የለውጥና መልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ በዘርፉ ከፍተኛ ክህሎትና እውቀት ባላቸው ባለሙያዎች ከሚያዚያ 25-27/2010ዓ.ም ድረስ በወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ስልጠና ሰጠ።

 MG 1815

አቶ አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በስልጠናው መክፈቻ ላይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት አምስት ዓመታት ከመጀመሪትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች በአፈጻጸሙ ከ1-3 ደረጃ እየወጣ እንደሚገኝ እና በአሁኑ ሰአትም ከ43000 በላይ ተማሪዎችን በስድስቱም ካምፓሶች ተቀብሎ እያስተማረ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

 MG 1635

ፕሬዚዳንቱ አክለውም የዚህ አይነቱ ስልጠና የአመራሩን እውቀትና ክህሎት በማሳደግ ዩኒቨርሲቲው እየሰጠ ያለውን የመማር ማስተማር፣የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን በጥራትና በትኩረት እንዲሰራ ስለሚያስችል ዩኒቨርሲቲውን በቀጣይ አመታትም ወደላቀ ከፍታ ያደርሰዋል ብለዋል።

(በስለሺ ነጋሽ)

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.