"ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል" በሚል መሪ ቃል የንባብ ሳምንት ተከበረ

IMG 3312

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር              "ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል" በሚል መርዕ ቃል ከመጋቢት 14-18/2010 ዓ.ም በሥነጽሁፍ ውጤቶች አውደ ርዕይ፤ የመጻሕፍት ሽያጭ ፤የስነ ጽሁፍ ምሽት እና የምክክር መድረክ ተካሄዷል፡፡

 MG 8689

ፕሮግራሙን አስመልክቶ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በተካሄደ የስነጽሁፍ ምሽትና የፓናል ውይይት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጅ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይ ፕሮፌሴር አለማየሁ ረጋሳ በደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንዳስታወቁት እንደዚህ ዓይነት ዝግጅቶች የተማሪዎችን የማንበብ ፍላጎት የሚያነሳሳና የመማር ማስተማሩን ሂዳት የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ በተለያዩ ደራሲያን የሚጻፉ መጽሕፊቶችን በመግዛት ህብረተሰቡ በንቃት እንዲያነብ የሚያበረታታ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው እንደሚደግፈው አስታውቀዋል፡፡

 

በዓውደ ርዕዩ ላይ ከመጻሕፍት ሽያጭ በተጨማሪ የንባብ ሳምንት እና ውይይት መድረኮች መካሄዳቸውንና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፤ የሀዋሳ ከተማ ማህበረሰብና የአካባቢው ኗሪዎች የተሳተፉበት ሲሆን፤ ደራሲ አንዱኣለም አባተ(የአፀደ ልጅ)፤ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋይል እና ደራሲ ጸጋዘዓብ ለምለም ተሞክሯቸውን አቅርበዋል፡፡

                                                           በዳዊት በዳሳ

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.