የሀዋሳ የኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀንን በደማቅ ሁኔታ አከበረ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ጾታና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ”የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሁሉም አካላት ጥረት ወሳኝ ነው ” በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ107ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ42ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም የሴቶች ቀን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ በ12/7/2010ዓ.ም በድምቀት አከበረ፡፡

 MG 8514

ዶ/ር ፍስሃ ጌታቸው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት በፕሮግራሙ ላይ የተገኙ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኃላ በዓሉን አስመልክተውም የዚህ ፕሮግራም አላማ ማተኮር ያለበት ተመሳሳይ ዕድል እና ዕኩልነትን ሴቶች እንዲቀዳጁ እንደሃገርም ሆነ እንደዩኒቨርሲቲያችን ተጨባጭ ሁኔታ መስራት ላይ ነው ካሉ በኃላ በዩኒቨርሲቲያችን የሴት ተማሪዎች ቁጥር 32% እንዲሁም ደግሞ የሴት መምህራን ቁጥር 14% የደራሰ ቢሆንም ወደፊት ከወንዶች እኩል በማመጣጠን 50% እስኪደርሱ ጾታን መሰረት ያደረገ አድሎን በማስወገድ መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

ወ/ሮ አርማዬ አሰፋ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮርፖሬት ኮሚውኒኬሽንና ማርኬቲንግ ዳይሬክቶሬት ተወካይ ዳይሬክተር በዕለቱ ተገኝተው ስለ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ታሪካዊ አመጣጥ አጭር ገለጻ ካረጉ በኃላ በዓሉን የማክበራችን ዋና አላማ ሴቶችን በትምህርታቸው ለማበረታታት፣እንዲሁም በማህበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎአቸውም ለማጠንከር፣ በተጨማሪም በስራ ድርሻቸውና ኃላፊነታቸው ላይ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ እውቅና በመስጠት በቀጣይ የተሻለ ስራ እንዲሰሩ ማስቻል ነው ብለዋል፡፡

ወ/ሮ አርማዬ አክለውም እኛ ሴቶችም እርስ በእርሳችን በመደጋገፍ እና በመተያየት በስራ ቦታ ላይ የእህትማማችነት መንፈስን በማዳበር እንዲሁም አንዳችን ለሌላችን እውቅናና ክብር በመስጠትየተሸለ ውጤት ልናስመዘግብ ይገባናል በማለት አሳስበዋል፡፡

በዕለቱም በትምህርታቸው ላቅ ያለ ውጤት ያመጡ ሴት ተማሪዎች፣ ትጉህ የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም የስርዓተ ጾታና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የሚሰራቸውን ስራዎች እንዲሳኩ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሴት የአስተዳደር ባለሙያዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የአከባበር ሁኔታዉን የሚገልጹ ተጨማሪ ቪዲዮ ይመልከቱ።

በስለሺ ነጋሽ

 

 

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.