የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከጀርመኑ ሆሄንሄይም ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የምርምር አውደ ጥናት አደረገ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከጀርመኑ ሆሄንሄይም ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር እያካሄደ በሚገኘውና በአየር ንብረት ለውጥ እና የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥን ላይ ባተኮረው CLIFOOD የተሰኘ ፕሮጀክቱ አካል የሆነ የምርምር አውደ ጥናት የድህረ-ምረቃ ትምህርት መርሃ-ግብር ትውውቅ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ አዳራሽ በህዳር 15/2010ዓ.ም አካሄደ።

አቶ አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በዕለቱ የተገኙትን እንግዶች እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት ለ5ኛ ጊዜ በአጠቃላይ አፈጻጸም በሃገሪቱ ከሚገኙ ነባር ዩኒቨርሲቲዎች ከ1-3 እንደወጣ፣ ባሉት 1,300 በላይ ምምህራን እና ከ6,000 በላይ የአስተዳደርና ጤና ባለሙያዎች ከ41,000 በላይ ተማሪዎችን በ 81 የመጀመሪያ ዲግሪ ፣በ 101 የሁለተኛና የሶስተኛ ዲግሪ መርሐ-ግብሮች እያስተማረና እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለውም ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ አገራት ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ማዕከላት ጋር ውጤታማ ግንኙነቶችና ትብብሮችን ተፈራርሞ እየሰራ እንደሚገኝና የዛሬውም CLIFOOD ፕሮጀክት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲና ሆሄንሄይም ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር የሚሰራ የኢትዮጵያና የጀርመን የቆየ የሁለትዮሽ ትብብር  ውጤት ነው በማለት ተጋብዘው የመጡት በዓለም አቀፍ ደረጃ በመስኩ ዕውቅ ምሁራን ልምዳቸውንና ዕውቀታቸውን ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ሊያጋሩ በመምጣታቸው ለጀርመን መንግስትና ለ DAAD ፕሮግራም ለዚሁ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዶ/ር ተስፋዬ አበበ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት በዓለማችን ላይ የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ እንደመሆኑ በአገራችንም ላይ በሚከሰቱት ለውጦች የምግብ ዋስትናን በተመለከተ ዩኒቨርሲቲያችን ጀርመን ከሚገኘው ሆሄንሄይም ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ሰፊ ምርምሮችን እየተደረገ ሲሆን ችግሩንም በዘላቂነት ለመፍታት ቀጣይ ስራዎችም ወደፊት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ዶ/ር ስንታየሁ ይገረም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ CLIFOOD ፕሮጀክት አስተባባሪም እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ ከ17 የዘላቂ ልማት አጀንዳዎች ውስጥ በሰባቱ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራና በአሁኑ ሰዓትም ለአስራ ሁለት የፒ ኤች ዲ ተማሪዎች ማለትም ስድስቱ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቀሪዎቹ ስድስት ደግሞ ጀርመን አገር በሚገኘው ሆሄንሄይም ዩኒቨርሲቲ እንዲማሩ የትምህርት ዕድል በፕሮጀክቱ የተሰጠ ሲሆን ተማሪዎቹም በምግብ ዋስትናና የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ዙሪያ ምርምሮችን እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

በዕለቱ የዶክትሬት ጥናት ዕቅዳቸውን በፖስተር ካቀረቡት ውስጥ መቅደስ ወ/ጊዮርጊስ እና ማርቆስ ቡዱሳ እንደገለጹት በዚህ ፕሮጀክት አማካይነት የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና የአየር ንብረት ለውጡን በመተንበይ ላይ ከፍተኛ ቴክኖሎጂን በመጠቀምና አካባቢያዊ ችግሮች ላይ በማተኮር ሰፊ ምርምሮች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ገልጸው ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ ያለው የአቅም ግንባታ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዕለቱ ፕሮፌሰር ዶ/ር ሬይነር ዶሉሽዝ የሆሄንሄይም ዩኒቨርሲቲ ምግብ ዋስትና ማዕከል ዳይሬክተርን ጨምሮ በርካታ የውጭ እና የአገር ውስጥ ተመራማሪዎች የተለያዩ ምርምሮችን እንዳቀረቡ ታውቋል።

 

ለበለጠ መረጃ https://www.daad.de/der-daad/daad-aktuell/en/59335-climate-change-and-food-security-research-seeks-new-answers/ ይመለልከ

 

                                                                                                                    በስለሺ ነጋሽ

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.