ዓለም አቀፍ የስራ ፈጠራ ሳምንት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ

ዓለም አቀፍ የስራ ፈጠራ ሳምንት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ህዳር 09/2010 ዓ.ም በድምቀት ተከበረ።

ዶ/ር ሙሉጌታ ዳዲ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በዕለቱ ተገኝተው እንደተናገሩት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር፣ ችግር ፈቺ ምርምሮችን ከማካሄድና የማህበረሰብ አገልግሎት ከመስጠቱ ባሻገር  የሚማሩት ተማሪዎች ተቀጥሮ ከመስራት በዘለለ ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ የስራ ፈጠራ የልቀት ማዕከል አቋቁሞ ተማሪዎቹን ንድፈ ሃሳባቸውን ወደ ተግባር የሚቀይሩበት የአሰራር ስርዓት የዘረጋ መሆኑን ገልጸው የዕለቱ መርሐ-ግብርም በዓለም አቀፍ ደረጃ የስራ ፈጠራ ሳምንት ሲከበር የዩኒቨርሲቲውን ተማሪዎች ከስራ ፈጠራ ጋር ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገለጸዋል።

ዶ/ር ሙሉጌታ አክለውም የዩኒቨርሲቲውን የ12 ወር የስራ ፈጠራ እንቅስቃሴ ስኬትና ተግዳሮቶች በዝርዝር ካቀረቡ በኋላ ለሰባት የፈጠራ ስራ ባለቤት ለሆኑ ተማሪዎች የገንዘብ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ሽልማቱ ለተማሪዎቹ የሞራል ድጋፍና ግብዓት ከመሆኑም በዘለለ ለሌሎች ተማሪዎችም ማነቃቂያ እንደሚሆን ገልጸዋል።

ተማሪዎቹም ዩኒቨርሲቲው ንድፈ ሃሳባቸውን ተቀብሎ፣ ቤተ-ሙከራዎችን በማመቻቸትና የተለያዩ ድጋፎችን ከዚህ በፊት እንዳደረገላቸው ገልጸው በዕለቱም ለስራዎቻቸው እውቅና ሰጥቶ ስላበረከተላአው ሽልማት የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ዩኒቨርሲቲውን አመስግነዋል።

በዕለቱ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ፊት ለፊት በተዘጋጀው ቦታ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ አስራ ሁለት የተለያዩ ዓለም አቀፍና ሃገር በቀል ድርጅቶች በበዓሉ ተገኝተው የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለጎብኝዎች ያስተዋወቁ ሲሆን በርካታ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት እንዲሁም የመገናኛ ብዙሐን የመርሐ-ግብሩ ታዳሚዎች እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይም የስራ ፈጠራንና ስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት በሚያደርገው ሁሉን ዓቀፍ እንቅስቃሴ ባለፈው ሚያዚያ 21/ 2009 ዓ.ም. ባደረገው የስራ-ዓውደ ርዕይ (job-fair) በርካታ ቀጣሪ ድርጅቶችንና ዓርአያ የሆኑ ስራ ፈጣሪዎችን በመጋበዝ የዓመቱን ተመራቂዎች ከስራ-ገበያውና ስራ ፈጠራ ጋር በሰፊው ማስተዋወቁ የሚታወስ ነው፡፡

                                                                                                    በስለሺ ነጋሽ

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.