የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ ደማቅ አቀባበል አደረገ

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የብሄር ብሄረሰቦች አሻራ ያረፈበት አንድነታችን መገለጫ ነው በሚል መሪ ቃል ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጥሪ የተደረገላቸው ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፣ የመንግስት መ/ቤት ኃላፊዎች፣ የዩንቨርሲቲው የስራ ኃላፊዎች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና ተማሪዎች በተገኙበት በህዳር 1/2010ዓ.ም ደማቅ የአቀባበል ስነ-ስርዓት ተደረገለት።

አቶ አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በዋንጫ አቀባበል ስነ-ስርዓቱ ወቅት የተገኙትን እንግዶች፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና የጤና ባለሞያዎች በራሳቸውና በዩኒቨርሲቲው ስም እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የተሰማቸውን ደስታ ከገለጹ በኋላ ሀገራችን ከድህነትና ከኋላ ቀርነት ተላቃ ከበለጸጉ ሃገሮች ተርታ እንድትሰለፍ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መገንባቱ ወሳኝ መሆኑን መንግስት በማመን የግድቡ ግንባታ በራሳችን ኃይል ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በተጠናከረ ሁኔታ እየተሰራ እንደሚገኝና ፕሮጀክቱም መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ በማስተሳሰር ከጫፍ እስከ ጫፍ እንዲተባበር እያደረገ ያለ ግዙፍ ህዝባዊ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለውም ፕሮጀክቱ አስተማማኝ የኃይል ፍላጎት ከማሟላት በተጨማሪ ከአካባቢያዊ ሃገራት ጋር የኢኮኖሚ ትስስር እንዲኖራቸው እንዲሁም የተረጋጋ ቀጠና እና የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዲጠናከር የራሱን ሚና የሚጫወት፣ ብሎም ሃገራዊ መግባባትን ከመፍጠሩም ባሻገር በተፈጥሮ ሀብታችን የመጠቀም መብታችንን በማረጋገጥ የኩራት ምንጭ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመቀጠልም ፕሮጀክቱ በተፋሰሱ ሃገራት የወደፊት ዕጣ ፋንታ ላይ አዎንታዊ እንድምታ ያለው፣ ኢትዮጵያ በራሷ ህዝብ በጀትና አቅም ግድቡን መገንባት መቻልዋ ከወዲሁ ፕሮጀክቱ የጂኦ ፖለቲክስ ማስከበሪያ መሳሪያ እየሆነ ማምጣቱን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም በህዝቡ ላይ የይቻላል መንፈስ ማስረጹን እንዲሁም  ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶችንም በራስ አቅም ማከናወን እንደሚቻል አንዱ ማሳያ ሲሆን የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂውን ተግባራዊ በማድረግም ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት አስረድተዋል፡፡ በመጨረሻም ዩኒቨርሲቲው በሃገራችን ካሉት አንጋፋ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ግንባር ቀደም ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ለሃገራችን የህዳሴ ጉዞ በመማር ማስተማር፣በምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት የበኩሉን አስተዋጽኦ ከማበርከትም በተጨማሪ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በአሁኑ ወቅትም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም የኢትዮጵያ ህዝብ አካል እንደመሆኑ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የበኩሉን ለመደገፍ ብር 30.2 ሚሊዮን በቦንድ ግዢና ስጦታ ማበርከቱን ተናግረው የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ላደረገው ርብርብም አመስግነዋል።

 

ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ አባል በዕለቱ ተገኝተው ሃገራችን ከዚህ ቀደም በታሪኳ በቀደሙት አባቶቻችን እና እናቶቻችን በከፈሉት መስዋዕትነት ነጻነትዋ ተከብሮ የቆየ ሲሆን የአሁኑ ትውልድ ደግሞ ከድህነት ራሱንም ሆነ ሃገርን ለማላቀቅ እያበረከተ ያለውን ሚና ገልጸውና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላበረከተው አስተዋጽኦ አመስግነው ወደፊትም በዚህ መሰሉ ሃገራዊ ፕሮጀክቶች በበለጠ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።                                                                

                                                                                       በስለሺ ነጋሽ

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.