በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲና በኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ትብብር የውይይት መድረክ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ ወቅታዊ የውጪ ግንኙነት እንቅስቃሴበሚል ርዕስ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና በኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ትብብር የውይይት መድረክ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ጳጉሜ 1 ቀን 2ዐዐ9 .. ተካሄደ፡፡

አቶ መለስ አለም የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በመርሐ-ግብሩ ላይ እንደተናገሩት የውጪ ግንኙነት እንቅስቃሴና ስራዎች መንግስት በሚመድበው መደበኛ በጀትና መስሪያ ቤት ብቻ የሚሰሩ ሳይሆኑ የሁሉንም ህብረተሰብ ተሳትፎና ተቋማት ርብርብ የሚጠይቁ ሲሆን ዩኒቨርሲቲዎችም ለዚህ መሰሉ እንቅስቃሴ የላቀ ድርሻ አላቸው ብለዋል፡፡

 

አቶ አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በዕለቱ የተገኙትን እንግዶችና ተሳታፊዎች እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መካከል የዚህ መሰሉ ውይይት ሲካሄድ በአይነቱ የመጀመሪያ እንደሆነ ገልፀው ዩኒቨርሲቲው ባለፉት አራት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተደረጉ የዩኒቨርሲቲዎች አፈፃፀም ውድድር መሰረት 1 - 3 በመውጣት ግንባር ቀደም እንደሆነና ከተለያዩ የውጪ ሀገሮች ጋር /4 በላይ /የጋራ ስምምነቶችን በማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ በእነዚህም እንቅስቃሴዎች የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርና በተለያዩ የዓለም አገራት የሚገኙ የአገራችን ሚሲዮኖች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ጠቅሰው በቀጣይም ዩኒቨርሲቲያችን ያነገበውን ታላቅ ራዕይ ለማሳካት በተመሳሳይ አስተዋጽኦው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

 

 

አምባሳደር መሃሙድ ድሪር ለተሳታፊዎች በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት ኢትዮጵያ በመካከለኛው ምስራቅ ካሉት ሃገሮች ጋር በታሪክ፣ በቋንቋ፣ በባህልና በሃይማኖት የረዥም ጊዜ ጥልቅ ትስስርና በህዝብ ለህዝብ ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እንዳላት ገልፀው የውጪ ጉዳይ ፖሊሲያችን በተለዋዋጭ ዓለም ውስጥ ሚናችንን በትክክል የምንገልፅበት በመሆኑ ፖሊሲዎቻችንም ቅልጥፍና የተሞላባቸው፣ በመላው የአገራችን ህዝቦችና በተለይም በትምህርቱ ማህበረሰብ የታወቁና በምርምርም የተደገፉ መሆን ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡ አክለውም ግብጽ የመካከለኛው ምስራቅ ሃገር ባትሆንም በአባይ ወንዝ ጉዳይ ላይ ታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ያላት አቋም የቅርብ ዲፕሎማሲያዊ ክትትልና ሰፊ ስራ የሚፈልግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 

አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ "ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገሮችና ከመካከለኛው ምሥራቅ ሀገሮች ጋር ያላት ግንኙነትና ለሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ያለው እንደምታ" በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጽሑፍ ላይ እንደገለጹትም ከጐረቤት ሃገሮች ጋር የምንመስርተው የውጪ ግንኙነት ለሃገር ደህንነትና ሴኩሪቲ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥና የጋራ ልማትና ተጠቃሚነትንም በከፍተኛ ደረጃ ከግምት ያስገባ መሆኑን ጠቅሰው ፖሊሲያችን ከውስጥ ወደ ውጪ የሚያይና ውስጣዊ ተግዳሮቶችን በመወጣት የውጪ ጉዳዮቻችን ማመቻቸትን ያማከለ ነው ብለዋል፡፡ የውጪ ሃገር ፖሊሲያችን የጐረቤት አገራትን ነባራዊ ሁኔታ በማጠጥናት የጋራ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ እንዲሁም ካለን የቆየ ትስስር የተነሳ ህዝቦቻችንን በተለያዩ ሃገራት የሚኖሩ አንድ ህዝቦች አድርጎ የሚመለከት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ሀገሮቻችን አንድም ብዙም ሲሆኑ ይህም በመሆኑ 1ዐዐ ሺህ በላይ ሱማሌያውያን፣ 16 ሺህ በላይ ኤርትራዊያንና 2ዐዐ ሺህ በላይ ሱዳናያውያን መጥተው ሃገራችን ውስጥ ልክ በሌላኛው ቤታቸው የሚኖሩ ያህል በነጻነትና በሰላም ይኖራሉ በማለት የገለፁ ሲሆን ከጐረቤቶቻችን ጋር የምንመስርተው ግንኙነት በመተማመንና ጥቅም ላይ የተሳሰረ በመሆኑ ታላቁ የህዳሴ ግድብን ለመገደብ ስናቅድ የሱዳን ከጐናችን መቆም ይህንኑ የግድብ እንቅስቃሴ ለማዳከም ያሰቡ ወገኖችን አቅም ያሳጣ ሆኗል ብለዋል፡፡

በዕለቱ አምባሳደር ታዬ አስቀስላሴ /በግብፅ የኢት-አምባሳደር/ በኢትዮጵያና በግብፅ ወቅታዊ ጉዳይ እንዲሁም አምባሳደር ነጋሽ ክብረት በጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት ቋሚ መልዕክተኛና በስዊዘርላንድ የሚገኙ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካይ "አገራችን በተለያዩ ዓለምአቀፍ መድረኮች ላይ እየተጫወተች ያለችው ሚናና ተደማጭነታችን" በሚል ሰፊ ማብራሪያ ያቀረቡ ሲሆን ከዩኒቨርስቲ ምሁራንና ከተሳታፊዎቹም በቀረቡት ጥናቶች ዙሪያ ውይይትና ጥያቄዎች ቀርበው በአቅራቢዎቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በመጨረሻም በውይይቱ ወቅት 50 በላይ ሚሲዮኖች የመጡ አምባሳደሮችና ቆንሲል ጄኔራሎች፣ ዲፕሎማቶች፣ የውጪ ጉዳይ ዋናው መስሪያ ቤት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞችና ተማሪዎች የተካፈሉ ሲሆን ይህን በዓይነቱን በአገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነ መርሐ-ግብር ለማዘጋጀት የተከበሩ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር / ወርቅነህ ገበየሁ፣ የቀድሞ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህርና በአሁኑ ወቅት በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጪ አገልግሎት ስልጠና ማዕከል ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር / ማርቆስ ተክሌና ሌሎችም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ ኃላፊዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በስለሺ ነጋሽ

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.