የፊቼ ጫምባላላ የሲዳማ ህዝብ የአዲስ ዘመን መለወጫ ክብረ በዓል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

ባለፈው ሰኔ 14 እና 15/2ዐዐ9 .ም የፊቼ ጫምባላላ የሲዳማ ህዝብ የአዲስ ዘመን መለወጫ በዓል በሀዋሳ ከተማና በሌሎችም አካባቢዎች በደማቁ መከበሩ ይታወሳል፡፡ ይህ በዓል በብሔሩ ተወላጆችና ወዳጆቻቸው ላለፉት በርካታ ዓመታት ሲከበር የቆየ ቢሆንም የአገራችን ህገ መንግስት ለሁሉም የአገራችን ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሁሉን አቀፍ ልማት በሰጠው ልዩ ትኩረት ዕውቅናው እያደገ በ2ዐዐ8 .ም በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና ባህል ተቋም በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል፡፡ ይህንኑ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ሀብት በጥናትና ምርምር እንዲሁም በተለያዩ መንገዶች ይበልጥ የማልማት ታሪካዊ አደራ ያለበት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምሁራኑ በግል ሲያደርጓቸው ከቆዩ ጥናቶችና ጥረቶች ባሻገር በዚህ ዓመት በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ታላቅ ሲምፖዚየም በማካሄድ በፊቼ ዕለት በሲዳማ የባህል አዳራሽ በየዓመቱ ከሚካሄደው ሲምፖዚየም በተጨማሪ አንድ በባህል ዙሪያ ሳይንሳዊ ውይይቶች የሚካሄድት ዕድልን አበርክቷል፡፡

ሰኔ 6/2ዐዐ9 .ም በዩኒቨርሲቲው የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በተካሄደው በዚሁ ሲምፖዚየም በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አቶ አያኖ በራሶ የመክፈቻ ንግግር የተደረገ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የሲዳማ ብሔርን ጨምሮ የሁሉንም የአገራችንን ብሔር ብሔረሰቦች እንዲሁም ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ያካተተ አንድ ቤተሰብ እንደመሆኑ እንዲህ ባሉ መርሐ-ግብሮች ያሉንን የጋራ እሴቶች እያበለፀግን እና የሚጠበቅብንንም ምሁራዊ ኃላፊነት እየተወጣን ልንቀጥል እንደሚገባ በዚሁ ንግግር ላይ ተጠቅሷል፡፡ የአገር ሽማግሌዎችም በምርቃት መርሐ-ግብሩን ያስጀመሩ ሲሆን ብዙ ችግሮችን ተጋፍጦ ለዛሬ የደረሰውን ቱባ ባህል ወጣቱ ትውልድ ሊንከባከበውና ለዓለም ሊያስተዋውቀው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በዕለቱ "የፊቼ- ጫንባላላ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ያስቻሉ እሴቶቹና በቀጣይ የህብረተሰቡ ሚና" በሚል ርዕስ ጥልቅ የሆነ ጥናታዊ ጽሑፍ በአቶ ታፈሰ ማቴዎስ የዩኒቨርሲቲው መምህርና የፒኤችዲ ተማሪ ቀርቦ በዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ታደሰ ቻቻሞ የሲዳማ ዞን ት/ት መምርያ ኃላፊ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚዳንት የመድረክ መሪነት ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ ይህ ዓይነት ሲምፖዚየም ቢያንስ በየዓመቱ እየተዘጋጀ የባህሉና በዓሉ ጥልቅ ፋይዳዎች የበለጠ ወደ ሳይንሳዊ መድረክ ሊመጡ እንደሚገባም በዕለቱ ከተሰጡ አስተያየቶች ለመረዳት ተችሏል፡፡

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Acting Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.