የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተቋማዊ ለውጥና መልካም አስተዳደር ምክር ቤት ከሰኔ 09- 10/2009 ዓ.ም ጉባኤ አካሄደ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተቋማዊ ለውጥና መልካም አስተዳደር ምክር ቤት ከሰኔ09- 10/2009 ዓ.ም በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጉባኤ አካሄደ። በጉባኤው የዩኒቨርሲቲው ሁለተኛ ዙር የዘጠኝ ወራት የመደበኛ፣ የተቋማዊ ለውጥና መልካም አስተዳደር ስራዎች አፈጻጸም የሱፐርቪዥን ማጠቃለያ ሪፖርት እና በስነምግባራዊ አመራርና ሙስናን መከላከል በሚል ርዕስ ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።
አቶ አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በጉባኤው መክፈቻ እንደተናገሩት የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቀዳሚ ዓላማዎች የትምህርት፣ የጥናትና ምርምር ስራዎች እና የማህበረሰብ አገልግሎት ሲሆኑ እነዚህን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ ዩኒቨርሲቲያችን የተቋማዊ ለውጥና መልካም አስተዳደር ስራዎችን ቁልፍ መሳሪያ አድርጎ በመጠቀም በስትራቴጂክ ዕቅዱ የተቀመጡ ግቦችን በማሳካት ለተከታታይ ዓመታት መሪ ከሚባሉ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ መሆኑን ለማሳየት ችለናል በማለት አሁንም ክፍተቶች እንዳሉብን በመገንዘብ ችግሮቻችንን ለይተን ለውጥ እንድናመጣ የአመራሩና የሰራተኛው ቁርጠኝነት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም የዩኒቨርሲቲው የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ኃላፊነታቸውን በመልካም ስነ ምግባርና ከሙስና በጸዳ መልኩ በመወጣት ለሃገርና ለህብረተሰብ እድገትና ልማት የሚያበረክቱትን አስተዋጽዖ ማሳደግ እንደሚገባና ሙስና ሃገርን ሚጎዳ በመሆኑ ሁላችንም የአገልጋይነት መንፈስ በመላበስ ወደክጣትና እርምጃ ከመድረሳችን በፊት በስልጠናው ግንዛቤ ጨብጠን በጋራ በመታገል ከሙስና የጸዳ ተቋም መገንባት ይኖርብናል ብለዋል።
በጉባኤው የመጀመሪያ ዕለት የዩኒቨርስቲው ተቋማዊ ለውጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑ አቶ ወንድሙ የሪፖርቱ ዓላማ በ2009ዓ.ም የዘጠኝ ወራት አፈጻጸምን በመገምገም በየስራ ክፍሎቹ በጥንካሬና በድክመት የታዩ ስራዎችን መለየትና አፈጻጸማቸውንም ለካውንስል አባላት ለውይይት ማቅረብ መሆኑን በመግለጽ በኮሌጆች፣ በኢንስቲትዩት፣ በዋናው ግቢ ዳይሬክቶሬትና ጽ/ቤቶች በመገኘት ክትትልና ድጋፍ በተደረገበት ወቅት የተስተዋሉ በጥንካራ፣ደካማ ጎኖችና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ያካተተ ማጠቃለያ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ቤቱም በሰፊው ተወያይቶባቸዋል።
በስነ ምግባራዊ አመራርና ሙስናን መከላከል በሚል ርዕስ ዙሪያ በዕለቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተጋበዙት ዶ/ር ፈንታ ማንደፍሮ ሰፋ ያለ ስልጠና የሰጡ ሲሆን በዩኒቨርስቲ ደረጃ ዩኒቨርስቲው ለመጀመሪያ ግዜ ተነሳሽነት ወስዶ ስልጠናውን እንዲሰጡ በመጋበዙ አመስግነው ስነምግባርና ትምህርተ ኃይማኖትን በተመለከተ አዲስ ባይሆንም ሁልግዜም በመደጋገም ትምህርትና ስልጠና እንደሚያስፈልግና መረዳት ብቻ ሳይሆን ልንኖርበት ይገባል ብለዋል።
በመጨረሻም በጉባኤው ወቅት የነበሩ ተሳታፊዎች የሁለት ቀን ቆይታቸውና ያገኙት ተሞክሮ መልካም እንደሆነና ቀጣይነት ቢኖረው ጥሩ እንደሆነ ገልጸዋል።
 

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Acting Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.