26ኛው የግንቦት 20 የድል በዓል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለ26 ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የግንቦት ሀያ የድል በዓል በዩኒቨርሲቲው የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በድምቀት አከበረ፡፡

በዋናው ግቢ የተካሄደውን በዓል በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ኢንጂነር ፍስሀ ጌታቸው እንደገለጹት የግንቦት ሃያ ድል በኢትዮጵያ ለዘመናት ተንሰራፍቶ የቆየውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች በዘላቂነት የቀረፈና አሁን ላይ አገሪቱ እያስመዘገበች ላለው ልማትና ዲሞክራሲ ዋነኛ መሰረት መሆኑን ጠቁመው ዩንቨርሲቲውም በድሉ የተገኙትን ለውጦች ቀጣይነት እንዲኖራቸው በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዶክተር ፍስሀ አያይዘው እንዳሉት በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ ጦርነት ከድህነት ጋር በመሆኑ ይህንን አስከፊ ጦርነት በድል ለመወጣት ሁሉም የዩንቨርሲቲው ማህበረሰብ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣና የተሻለችና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለነገው ትውልድ ማስተላለፍ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በበዓሉ ላይ ተገኝተው ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት የኢፌዴሪ የፌዴራልና አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስቴር የምርምር ልማትና ሪሶርስ ሞቢላይዜሽን ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ሻንቆ ደለለኝ በበኩላቸው “የኢትዮጵያ ፌዴራል ስርዓት ባህሪያት፣ የዴሞክራሲያዊ ሕብረ-ብሄራዊ አንድነት ግንባታ ሂደት፣ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች” በሚል ርዕስባቀረቡት የውይይት ሰነድ የግንቦት 20 ትሩፋት የሆነው የአሁኑ ህገ-መንግስታችንን መሰረታዊ እሴቶች እና እያጋጠሙት ያሉትን ተግዳሮቶች ፍጹም ለከፍተኛ ት/ት ማህበረሰብ በተቃኘ አግባብ አቅርበው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በዘርፉ በሰፊው እንዲመራመር፣ እንዲከራከርና ለአገር የሚበጅ ማንኛውንም የተሻለ ሀሳብ እንዲያቀርብ አሳስበዋል፡፡ በወቅቱ አወያይ የነበሩ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ሰብሳቢ የተከበሩ ረአቶ ሚሊዮን ማቲዎስም በበኩላቸው ሁሉም ማህበረሰብ በየግልና እንደተቋም የተለያዩ የዕድገትና ልማት ዕቅዶች ያሉት መሆኑ አሌ የማይባል ሀቅ ሲሆን ይህን እውን ለማድረግ ግን ሀገር የተሰኘችን የጋራ ቤት በጋራ ለማልማትና በተለይም ሰላሟንም ሆነ ዴሞክራሲያዊነቷን ለማረጋገጥ ያለው ቁርጠኝነትና መሰጠት ሊደርስ ከሚገባው ደረጃ የደረሰ እንዳልሆነ ጠቁመው ሁሉም በቤትም ሆነ በሚገኙ መድረኮች ሁሉ የአገርን ሰላም፣ ልማትና በህገ-መንግስት ላይ የተመሰረተ ጤናማ ዕድገትን ለማረጋገጥ ግንባር ቀደም ሆኖ ሊቆም እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በመጨረሻም በዋናው ጊቢ መድረክ ሰፊ ውይይት በዩኒቨርሲቲ ማህበረሰቡ የተካሄደ ሲሆን በቀጣይም በርዕሱ ሳይንሳዊ የሆኑ ኮንፈረንሶች እየተዘጋጁ የከፍተኛ ት/ት ተቋማት በዘርፉ ያላቸውን ሚና ሊያጎሉ እንደሚገባ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን በዓሉ በሁሉም የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች በርካታ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በተገኘበት በቀረቡ ጥናታዊ ጽሑፎች ላይ በመወያየት በደማቅ መርሐ-ግብር እንደተከበረ ለመረዳት ተችሏል፡፡

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Acting Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.