የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት 30ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት 30ኛ መደበኛ ጉባኤውንበሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት አስተናጋጅነት ከ35 የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች አባል ህብረቶች ጋር ከየካቲት 24-26 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተሳካሁኔታ ካሄደ፡፡

ዶ/ር መሳይ ሃይሉ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአስ/ተ/አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት መንግስት ለከፍተኛ ት/ት ተቋማት የሚሰጠው እገዛ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽየተማሪዎች ህብረትም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማሩ ሂደት በሰላም እንዲካሄድ ከፍተኛድርሻ እንዳለውም ተናግረዋል።

ተማሪ ማኸኝ ድጋፉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት እንደተናገረውትምህርት የዕድገትና እና ልማት መሰረት በመሆኑ የሃገራችንን ማህበራዊ፤ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማፋጠን ጉልህ ሚና እንዳለውና የኢትዮጵያ ከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ኢትዮጵያ ውስጥ በ35 ዩኒቨርሲቲዎች ካሉ አባል ህብረቶች የተገነባና በሃገሪቱ በሚከናወኑ ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የጎላ ሚና የሚጫወት አደረጃጀት ነው ብለዋል፡፡

ህብረቱ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ በትጋት የሚሰሩ አመራሮችን እያፈራ፤ በሃገራችን ለሚካሄዱ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች በቀጥታ በመሳተፍ እና ህብረቱ የ"All Africa Student Union" አባል በመሆኑ አፍሪካ ለምታደርገው ሁለንናዊ የዕድገት ጥረት የበኩሉን አስተዋጾ የሚያደርግ እንደሆነ የህብረፕሬዚዳንት በመግለጽ ህብረቱ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል የዩኒቨርሲቲዎች ሁለንናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስቧል።ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲለጉባኤው መሳካት ላደረገው አስተዋጾ የላቀ ምስጋና አቅርቧል፡፡

በመቀጠልም ከ35 ዩኒቨርሲቲዎች በመጡ የህብረቱ አባላት የስድስትወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርትና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ በመነጋገር ስለህብረቱ ዌብሳይት፤ ስለ ጸረ-ሱስና ተያያዥ ጉዳዮች በጋራ በመወያየት ጉባኤው ተጠናቋል፡፡

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Atkilt Esaiyas
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.