የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ሁሉም ፈፃሚ አካል ራሱን በጥልቀት መፈተሽ እንዳለበት ተጠቆመ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመምህራንአስተዳደር ሰራተኞች ጥልቅ ተሃድሶ መድረክ ከየካቲት 24-28 ቀን 2009.በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሄደ።

በመድረኩ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ሰብሳአቶ ሚሊዮን ማዎስ እንደገለጹት ሀገራችን እያስመዘገበች ያለውን የዕድገትና ልማት ውጤቶች አጠናክሮ ለመቀጠልና ከድነት ለመላቀቅ ሚደረገውጥረት ለማገዝ  በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት ፈጻሚ አካላት ሚና ከፍተኛ ነው።በመሆኑበዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ሁሉም ፈፃሚ አካላት እራሳቸውን በጥልቀት መመልከት አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

የተሃድሶ መድረያስፈለገበትዋነኛው ዓላማም ሲገልጹ፤ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች በአንድ ዓላማ በመንቀሳቀስ ዩኒቨርሲቲውብቁ ዜጋ የማፍራት ግብ በሚገባ ማከናወን እንዲቻል፤ በተጨማሪመደበኛ ስራዎቸውን ከምጊዜውም በበለጠ በአገልጋይነት መንፈስ እንዲያከናውኑ ለስቻል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዳንት አቶ አያኖ በራሶ በበኩላቸው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት ወደ 40 ሺ የሚጠጉ አጠቃላይ ተማሪዎች ያሉት መሆኑን ገልፀው ላለፉት ሁለት ዓመታት በዩኒቨርሲቲው በተፈጠረው የልማት ሰራዊት አደረጃጀት የተሻራ ማከናወን መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

አራት ቀናት በተካሄደው የጥልቅ ተሃድሶ ድረክ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞችና መምህራን የተሳተፉ ሆን ከበላይ አመራሩ ጀምሮ በየሥራ ክፍሉ በተካሄደው የሂስ ግለሂስ መድረክም እያንዳንዱ ፈጻሚ ደካማና ጠንካራ ጎኖቹን ቅሶ በማውጣት ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ የተሻራ ለመስራት ተነሳሽነመኖር እንዳለበት ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

ግምገማውለእያንዳንዱ ፈጻሚ ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ ደረጃ የራ አፈፃፀም ውጤት ተሰጥቷል። በቀጣይም ለደረጃ ዕድገትም ሆነ ለአፈጻፀም ልት የደረጃ ምደባው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ ተገልጾአል፡፡

በተመሳሳይም የተማሪዎች መድረኮች የተካሄዱ ሲሆን አገራችን በአሁኑ ወቅት ያለችበት ተጨባጭ ሁኔታና ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የሚጠበቀው ተጨባጭ አስተዋጽኦ ላይ የጋራ መግባባትና ቁርጠኝነት የተያዘባቸው መድረኮች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በኮኮማዳ ሪፖርተሮች    

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Acting Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.