የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የስርዓተ-ጾታ ዳይሬክቶሬት አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በድምቀት አከበረ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የስርዓተ-ጾታ ዳይሬክቶሬት በአለም አቀፍ ደረጃ ለ108ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ38ኛ ጊዜ የተከበረውን አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን መጋቢት 2/2006 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የስልጠና ማዕከል አክብሯል፡፡

01በዓሉን አስመልክቶ የተማሪዎችና አስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ አያኖ በራሶ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ እለቱ የሀገራችን ሴቶች በህገ-መንግስቱና በሌሎች ህጎች የተረጋገጡላቸውን መብቶች ለማስከበር የትግል አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበትና በሀገሪቷ በሚካሄደው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በጋራም ሆነ በተናጠል ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለመሆን ትግላቸውን ሚያጠናክሩበት ዕለት ነው ብለዋል፡፡ አቶ አያኖ አክለውም ይችን ሀገር ከድህነትና ኋላ ቀርነት የምናላቅቀው ሴቶች ከወንዶች እኩል ወደ ትምህርት ቤት ሲገቡና በየዘርፉ ተጠቃሚ ሲሆኑ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዓሉ በተከበረበት ዕለት ከሴቶች ቁጥር ይልቅ የወንዶችቹ ከፍ ማለቱ ደግሞ ወንድ ተማሪዎች ለሴቶች መብት መከበር ታጥቀው መነሳታቸውን ያሳያል ብለዋል፡፡

ሲስተር ትዕግስት ከበደ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የስርዓተ-ጾታ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር ማርች 8ን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ እሳቸው እንዳብራሩት የዚህ በዓል መከበር ዋነኛ ዓላማ በአለም ላይ ያሉ መንግስታት የሴቶች ጉዳይ የልማት የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ እንደሆነ አምነው በመቀበል በሴቶች ዙሪያ ፖሊሲዎቻቸውን በመፈተሽ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ መድሎዎችን እንዲያስወግዱና የሴቶችን እኩል ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት እንዲያረጋግጡ ለማነሳሳት ነው ብለዋል፡፡

003ሲስተር ትዕግስት አክለውም በአለም ላይ ያሉ ሴቶች በድንበር፣ በሀይማኖት፣ በቀለም፣ በቋንቋና በባህል ሳይለያዩ የሚደርስባቸውን ጭቆናና መድልኦ የሚያወግዙበት፣ አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበት፣ ድምጻቸውን በጋራ ሚያሰሙበት፣ ለነጻነትና ለፍትህ ያደረጉትን ተጋድሎ የሚዘክሩበት፣ ልምድ የሚለዋወጡበትና ለበለጠ ትግል ተቀናጅተው ለመንቀሳቀስ ቃል የሚገቡበት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

አንዳንድ ያነጋገርናቸው ተማሪዎችም  የበዓሉ መከበር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልጸው  ከስርዓተ-ጾታ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ባሻገር ጠንካራ የሆነ የዩኒቨርሲቲው ሴት ተማሪዎች ክበብ አለመኖሩን እንደ ችግር አንስተዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ስልጠና ማዕከል ለግማሽ ቀን በተካሄደው በዚህ ታሪካዊ ቀን የዩኒቨርሲቲው የበላይ ሃላፊዎች፣ መምህራንና ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

 

በወንድማገኝ ተስፋዬ

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Atkilt Esaiyas
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.